(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ፣ ሞስኮ በሁለቱ ሀገራት መካከል ለሚደረጉ ማናቸውም የሰላም ድርድሮች አስፈላጊውን እገዛ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ሰርጌይ ራያብኮቭ አስታወቁ።
ምክትል ሚኒስትሩ አክለውም ሩሲያ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት ቢኖራትም፣ ፍላጎቷን ግን በሁለቱ ወገኖች ላይ በግድ የመጫን እቅድ እንደሌላት በግልጽ ተናግረዋል።
ሰርጌይ ራያብኮቭ ከሀገሪቱ የመንግስት የዜና ወኪል ታስ (TASS) ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ፣ "ይህንን ግጭት ለመፍታት ሩሲያ ሊደረግ የሚችለውን ሁሉንም ዓይነት ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን ተፋላሚዎቹ ወገኖች በሚገባ ያውቃሉ። በተመሳሳይ ጊዜ እኛ አገልግሎታችንን በነሱ ላይ በፍጹም ጭነን አናውቅም፤ የመጫንም ፍላጎት የለንም። ነገር ግን ተገቢው ጥያቄ ከቀረበልን የመርጃ እጃችንን እንዘረጋለን" ብለዋል።
ምክትል ሚኒስትሩ ሞስኮ ሁልጊዜም ቢሆን ለችግሮች መፍትሄ የሚገኘው በፖለቲካዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገዶች ብቻ ነው የሚል ፅኑ እምነት እንዳላት እና አሁንም ለዚህ ቁርጠኛ መሆኗን አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ዋሽንግተን እና ቴህራን የድርድር ሂደቱን ለመቀጠል እያደረጉ ያሉትን ሙከራዎች ሩሲያ እንደምትደግፍ የገለጹት ራያብኮቭ፣ በተለይም በአካባቢው መረጋጋት እንዲሰፍን እና ለዘላቂ ሰላም ምቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ለማድረግ የፓኪስታን ወገን እያጫወተ ያለውን ንቁ እና አዎንታዊ ሚና አድንቀዋል።

5 months ago