በዳታ ሉዓላዊነት ዙሪያ የተከናወኑ ስራዎች የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል ሊያገለግሉ ይገባል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዳታ ሉዓላዊነት ዙሪያ የተከናወኑ ስራዎች የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለመለወጥ ሊያገለግሉ ይገባል አሉ።
''የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት'' በሚል መሪ ሀሳብ ኢትዮጵያ በመረጃና በስታቲስቲክስ የሉዓላዊነት ጉዞ ባስመዘገበችው ስኬት ላይ ያተኮረ ሀገራዊ ጉባኤ ተካሂዷል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመድረኩ ላይ፤ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በሳተላይት፣ በድሮንና በጂኦስፓሻል መረጃ የታገዘ ዘመናዊ አሰራርን መዘርጋቱ ለመላው ኢትዮጵያውያን ታላቅ ድል ነው ብለዋል።
በርካታ ሺህ ሰዎችን በማሰማራት የተሰበሰቡ መረጃዎችና ጥቅም ላይ የዋሉ ሳይንሳዊ ዘዴዎች ለሀገሪቱ ቀጣይ እድገትና ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ጉልህ ሚና እንዳላቸው ጠቁመዋል።
በጥቂት ሀገራት ብቻ የሚታየውን የመረጃ አሰባሰብ፣ የትንተና እና የአቀራረብ ዘዴ በሀገር በቀል ባለሙያዎች ማየት መቻሉ ትልቅ የኩራት ምንጭ መሆኑንም ነው የገልጹት።
በመረጃ አሰባሰብ ሂደት ውስጥ በመስክ ላይ የሚሰበሰብ ተጨባጭ መረጃ የላቀ ዋጋ እንዳለው በማንሳት፤ የተሰበሰበው ዳታ በፖሊሲ ተደግፎና አመራር ተሰጥቶት ወደ ተጨባጭ ውጤት መሸጋገር ይገባዋል ነው ያሉት።
የተሰበሰበው ዳታ የመጨረሻ ግብ የእያንዳንዱን ሰው ህይወት መንካት፣ ማሻሻል እና ውጤት ማምጣት እንደሆነ ጠቅሰው፤ የሰው ህይወት መለወጡን ማረጋገጥ እንደሚገባ አመልክተዋል።
አርሶ አደሩ ከማምረት ባለፈ ልጆቹን ሲያስተምር፣ ህጻናት በምግብ እጥረት እንዳይጎዱ ሲደረግ እንዲሁም ይህንኑ እንደ ሀገራዊ ኢንቨስትመንት የሚገነዘቡ ዜጎች ሲበራከቱ መረጃው እውነተኛ ፋይዳውን አገኘ ማለት እንደሆነም አብራርተዋል።
በዮናስ ጌትነት

18 days ago