(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዘለንስኪ ‹‹ዛሬ በ524 ድሮንና በ22 ሚሳኤል ተደብድበናል›› አሉ፡፡ የዩክሬይኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ በዛሬው እለት ከሩሲያ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ገለፁ፡፡ ፕሬዝደንቱ በኤክስ ገፃቸው ላይ ‹‹ሩሲያ ዛሬ በድኒፕሮና አካባቢው የፈፀመችው ድብደባ 6 ሰአታትን የፈጀ ነበር፡፡ አንድ ሚሳኤል በመኖሪያ አፓርትመንት ብሎክ ላይ ጉዳት ሲያደርስ ሌሎች ሚሳኤሎች ደግሞ ሲቪል መሰረተ ልማቶች በከፍተኛ ሁኔታ መተዋል፡፡ ጥቃቶቹ በክልሉ ውስጥ ያሉ የሀይል ተቋማትን ኢላማ ያደረጉ ነበሩ›› ብለዋል፡፡
ጨምረውም በኦዴሳ ወደብ ላይም በድሮን ከፍተኛ ጥቃት መፈፀሙን ገልፀው አንድ ድሮን በወደቡ ቆሞ የነበረን የቻይናን መርከብ መምታቱንም አስረድተዋል፡፡ ሩሲያዊያን የቻይናን መርከብ ሆነ ብለው እንደመቱት ለመግለፅም ‹‹በወደቡ ላይ የማን መርከብ እንደቆመ አያውቁም ብዬ አላስብም›› ብለዋል፡፡ በአጠቃላይ በ8 ግዛቶች ላይ የንብረት ውድመት መድረሱን ገልፀው በአስራዎች የሚቆጠሩ መቁሰላቸውን የጠቀሱት ዘለንስኪ ሲቀጥሉም ‹‹በዛሬው ጥቃት ሩሲዊያን 524 ድሮኖችንና 22 የተለያየ አይነት የባለስቲክና ክሩዝ ሚሳኤሎችን ተጠቅመዋል፡፡
አሁንም በመላው አገሪቱ ውስጥ የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂያ ደወሎች እየተሰሙ ነው፡፡ የአየር መቃወሚያችን የደህንነት ሁኔታው በሚፈቀድለት ልክ እየሰራ ይገኛል›› በማለት አስረድተዋል፡፡ በማስከተልም ‹‹ሩሲያ በሰዎች ላይ ጥቃት የምታደርሰው በባለስቲክ ሚሳኤሎቿ ተመርኩዛ ነው፡፡ ስለዚህም እኛ አውሮፓዊያን ይህንን ጥቃት ለመከላከል የቻልነውን ያህል ጥረት ማድረግ አለብን፡፡ አውሮፓ የራሷ ፀረ ባለስቲክ ሚሳኤል ሊኖራትና ራሷን ለመከላከል የሚያስችል በቂ አቅም ልታዳብር ይገባል›› ብለዋል፡፡

1 month ago