Logo
EBC
‎መረጃ የዚህ ዘመን ስትራቴጂካዊ ሀብት እና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የሚገነባበት ቁልፍ የሉዓላዊነት ምሰሶ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
****************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት" በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው ሀገራዊ ጉባኤና ኤግዚቢሽን ላይ በመገኘት፣ ኢትዮጵያ በመረጃና በስታቲስቲክስ የሉዓላዊነት ጉዞ ያስመዘገበችውን ትልቅ ድል እና በዘርፉ የታየውን እመርታ ተመልክተው አድንቀዋል፡። ‎

‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባስተላፉት መልዕክት፤መረጃ የዚህ ዘመን ስትራቴጂካዊ ሀብት እና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የሚገነባበት ቁልፍ የሉዓላዊነት ምሰሶ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የተዋሰ አሊያም በውጭ አካላት ላይ ጥገኛ የሆነ መረጃ ሀገራዊ መሻትን ማሳካት ስለማያስችል የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የራስን መረጃ በራስ አቅም መሰብሰብ እና መተንተን ወሳኝ ግብዓት እንደሆነ አስገንዝበዋል።

አክለውም የመረጃ አሰባሰብና ትንተና ሥራው በሀገር ልጆች እውቀትና ክህሎት ሲከወን ማየት ታላቅ ሀገራዊ ኩራት መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ወደፊትም የመረጃ ትኩረታችን በቁጥር በሚገለጹ ውጤቶች ላይ ብቻ ሳይሆን ሰው ተኮር በሆኑና በዜጎች ሕይወት በሚታዩ ተጨባጭ ለውጦች ላይ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።
#datasovereignty #policyindependence #ethiopia #pmabiyahmed #ethiopianbroadcastingcorporation

18 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.