(ዘ-ሐበሻ ዜና) ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለምርጫ ቅስቀሳ በቀን እስከ 143,000 ብር እያወጡ መሆኑን ተናገሩ፡፡ 15 ቀናት ለቀሩት 7ተኛው አገራዊ ምርጫ ገዢውን ፓርቲ ጨምሮ ተወዳዳሪዎች በተለያየ መንገድ ቅስቀሳ እያከናወኑ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁንና ተቃዋሚ ፓርቲዎች በዚህ የምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት የተለያየ ፈተናዎች እያጋጠማቸው መሆኑን በመናገር ላይ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል ኢህአፓን ጨምሮ 4 ፓርቲዎች ያቀፈው ትብብር አንዱ ነው፡፡
የኢህአፓ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አብርሀም ሀይማኖት ትብብሩን ወክለው እንደገለፁት እያጋጠማቸው ያለው ፈተና ዘርፈ ብዙ ነው፡፡ ሲናገሩም ‹‹ከምርጫ ቦርድ የምናገኘው ገንዘብ እያነሰ ከመምጣቱም በላይ ከህዝብ የሚገኘው ድጋፍም ቀንሷል›› ብለዋል፡፡ አቶ አብርሀም ለፎርቹን ጋዜጣ እንደተናገሩት ህዝቡ ከሰላማዊ ፖለቲካ እየራቀ ሲሆን ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ተቃዋሚዎችን መደገፍ ለብዙዎች ስጋት የሚፈጥር እየሆነ መምጣቱ ነው፡፡
በዚህ የተነሳም ዜጎች ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ብቻም ሳይሆን ለምርጫ ቅስቀሳ አዳራሽና መኪና ለማከራየት እየፈሩ መሆናቸው ሰላማዊ የፖለቲካ ምህዳሩን እንዳጠበበው አስታውቀዋል፡፡ ለምርጫ ቅስቀሳ የመኪናና ሳውንድ ሲስተም ኪራይ ዋጋ፣ የህትመትና የነዳጅ ዋጋዎች ጭምር መናራቸው ሌላኛው ፈተና መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ አቶ አብርሀም እንደሚገልፁት ኢህአፓ በአሁኑ ወቅት ለምርጫ ቅስቀሳ በቀን 143,000 ብር እያወጣ ይገኛል፡፡ ከምርጫ ቦርድ ያገኙት ደግሞ እንደፓርቲ 800,000 ብር እና ለእያንዳንዱ እጩ 7,000 ብር መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ሲናገሩም ‹‹በነዳጅ ስርጭት ላይ የተፈጠረው መስተጓጎል ለምርጫ ቅስቀሳችን ነዳጅ ለማግኘት አስቸግሮናል፡፡›› በማለት ገልፀዋል፡፡
ለዘንድሮው ምርጫ ከ50 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን ምርጫ ቦርድ ያስታወቀ ሲሆን በምርጫው ላይ 47 ፓርቲዎች እንደሚሳተፉም መግለፁ ይታወቃል፡፡ ለቦርዱ 10.5 ቢሊዮን ብር በጀት ተይዞለት የነበረ ቢሆንም ተጨማሪ ገንዘብ ጠይቋል፡፡ በምርጫው ላይ በአጠቃላይ 10 933 እጩዎች ለመሳተፍ ተመዝግበዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 2950 ያህሉ ወይንም 27 ፐርሰንቱ የብልፅግና እጩዎች ሲሆኑ በቀጣይነት 1256 ፓርቲዎችን ኢዜማ በማስመዝገብ ይከተላል፡፡ ትብብር ደግሞ 1032 እጩዎችን አስመዝግቧል፡፡

5 months ago