የእስራኤል ጦር አዲስ የድሮን ስጋት ገጠመው፤ ከዩክሬን ጋር ለመተባበር እያሰበ ነው
ሄዝቦላህ በፋይበር ኦፕቲክ የሚታዘዙ አዳዲስ ድሮኖችን መጠቀም መጀመሩ በእስራኤል መከላከያ ሰራዊት (IDF) ላይ ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩን Jerusalem Post ዘግቧል። ይህ ስጋት እስራኤል በዘርፉ ሰፊ ልምድ ካላት ዩክሬን ጋር እንድትተባበር ግፊት እያደረገባት ይገኛል።
እነዚህ FPV ድሮኖች በፋይበር ኦፕቲክ ገመድ አማካኝነት ከኦፕሬተሩ ጋር የተገናኙ በመሆናቸው በኤሌክትሮኒክ መዝጊያ መሳሪያዎች ለማሰናከል የማይቻል እና በራዳር ለመለየት እጅግ አስቸጋሪ ናቸው።
ባለፈው እሁድ በሊባኖስ ድንበር አቅራቢያ በደረሰ የዚህ አይነት ድሮን ጥቃት አሌክሳንደር ግሎቫንዮቭ የተባለ የ47 ዓመት የእስራኤል ተጠባባቂ ወታደር ተገድሏል።
ይህ የድሮን ቴክኖሎጂ በዩክሬን የጦር ግንባር በስፋት ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን፣ ሄዝቦላህ ስልቱን ከዚያው እንደቀሰመው ይታመናል።እስራኤል፣ አሜሪካ እና ሌሎች አጋሮች ከዩክሬን ጋር በመሆን እነዚህን ድሮኖች ለመመከት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን በጋራ ለማልማት እያሰቡ ነው።
seledadotio

5 months ago