Logo
EBC
ትራምፕ እና ሺ ቤጂንግ ላይ ሲገናኙ ዓለም አዲስ የሰላም መልሕቅ ይጠብቅ ይሆን?
********************

በታሪካዊው ቲያንአንመን አደባባይ ዙሪያ የደኅንነት ጥበቃው ተጠናክሯል፤ ቤጂንግም የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ለመቀበል በደማቅ ድባብ አጊጣለች።

ከዓመታት በኋላ የተሳካው ይህ የሁለቱ ኃያላን መሪዎች ጉባኤ፣ ከንግድ ጦርነት እስከ ታይዋን ውጥረት፣ ከቴክኖሎጂ ፉክክር እስከ መካከለኛው ምስራቅ ሰላም ድረስ ያሉ ዓለም አቀፍ አጀንዳዎችን በጠረጴዛው ዙሪያ አምጥቷል።

የኢኮኖሚ መረጋጋት የሚፈልጉት ሺ ጂንፒንግ እና ብሔራዊ ጥቅማቸውን ያስቀደሙት ትራምፕ፣ በቤጂንግ የሚያደርጉት ቆይታ ለሚቀጥሉት ዓመታት የዓለምን ጂኦ-ፖለቲካዊ አቅጣጫ እንደሚወስን ይጠበቃል።

ታላላቅ የዓለም ኩባንያዎች መሪዎች ጭምር የሚታደሙበት ይህ ጉብኝት፣ በከፍተኛ ቴክኖሎጂ እና በንግድ ትስስር ረገድ አዲስ ስምምነት ይዞ ይመጣ ይሆን?

የጉብኝቱን ዝርዝር መረጃዎች፣ የተነሱ ዋና ዋና አጀንዳዎችን እና ለዓለም ኢኮኖሚ ያለውን ፋይዳ አስተያየት መስጫው ውስጥ ባለው ሊንክ ያንብቡ።
#addisababa #globalpolitics #trumpchinasummit #beijing2026

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.