(ዘ-ሐበሻ ዕይታ) የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ስለአሜሪካ ህግ እና አሰራር ሲናገሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በየስቴቱ እንደሚኖሩ ይዘነጉታል፣ ወይም በንቀት ወይም በትዕቢት ባለማወቅ ፣ ማንም አይገነዘብም በሚል ስሜት የሚናገሩ ይመስለኛል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሃይማኖት ዘለቀ፣ ሚዲያዎች "ብሔራዊ ጥቅምን" ስለማስጠበቅ እና የውጭ "ጠላት አጀንዳን" ስለማራመድ ያነሱት ሀሳብ አነጋጋሪም በብቃታቸውም ላይ የሚያስተዛዝብ ጥቁር ነጥብን ጥሎ ያለፈ ይመስለኛል። ዋና ዳይሬክተሯ መንግስት የሚዲያ ፈቃድን ለመሰረዝ ያለውን እርምጃ ሲያጸድቁ፣ የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን እንደ ማሳያ ጠቅሰዋል። ትራምፕ "ብሔራዊ ጥቅም በተነካ ጊዜ ሬጉላተሪ ቦርዱን አልፈው የሚዲያ ፈቃድ ሪቮክ አድርገዋል (ሰርዘዋል)" በማለት የተናገሩት ቃል ግን ከእውነታው የራቀ እና ለፕሬስ ነፃነት አፈና እንደ ማመካኛ የቀረበ የተሳሳተ ትርክት ነው።
የዋና ዳይሬክተሯን የትራምፕ ማነፃፀሪያ ስንፈትሸው፣ ንግግራቸው መሰረተ ቢስ መሆኑን እንረዳለን። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በስልጣን ዘመናቸውም ሆነ በአሁኑ ወቅት እንደ ኤንቢሲ እና ኤቢሲ የመሳሰሉ ተቋማትን "የሐሰት ዜና አሰራጫችኋል" በሚል የብሮድካስት ፈቃዳቸው እንዲሰረዝ በተደጋጋሚ ዛቻዎችን ማሰማታቸው እውነት ነው። ነገር ግን በአሜሪካ ህገ-መንግስት አንደኛ ማሻሻያ (First Amendment) የፕሬስ ነፃነት ጥበቃ ምክንያት፣ ትራምፕም ሆኑ የኮሙኒኬሽን ተቆጣጣሪው ኤፍሲሲ በዜና ይዘት ወይም በመንግስት ላይ በሚቀርብ የፖለቲካ ትችት ምክንያት የማንንም የብሮድካስት ሚዲያ ፈቃድ ሰርዘው አያውቁም። የትራምፕ አስተዳደር በቅርቡ በኢራን ጦርነት ዘገባዎች ዙሪያ በሚዲያዎች ላይ ጫና ለማሳደር ቢሞክርም፣ ተቋማቱ በህግ አግባብ እየተሟገቱ እንጂ ፕሬዝዳንቱ ቦርዱን አልፈው በግላቸው የዘጉት የቴሌቪዥን ወይም የሬዲዮ ጣቢያ የለም። ትራምፕ የነጩ ቤተመንግስትን ጋዜጠኞች የመግቢያ ባጅ (Press Pass) ከልክለው ያውቁ ይሆናል እንጂ፣ የአንድን ሚዲያ ህጋዊ የብሮድካስት ፈቃድ አልሰረዙም። ዳይሬክተሯ ይህንን ያልተፈጸመ እና በህግም የማይቻል የትራምፕን ዛቻ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚወሰድ የሚዲያ አፈና እንደ ትክክለኛ የህግ ማዕቀፍ አድርገው ማቅረባቸው ትልቅ የእውነታ ቅጥፈት ነው።
ከእውነታ ቅጥፈቱ ባሻገር፣ ሃይማኖት ዘለቀ ያነሱት "የብሔራዊ ጥቅም" እና "የጠላት አጀንዳ" ትርክት እጅግ አሳሳቢ እና ኋላ ቀር የሆነ የሚዲያ ቁጥጥር እሳቤን የሚያንፀባርቅ ነው። አገራዊ መግባባት እና ሉዓላዊነትን ማስጠበቅ አስፈላጊ ቢሆንም፣ "ብሔራዊ ጥቅም" የሚለው ሐረግ ገዥ ፓርቲዎች ራሳቸውን ከትችት ለመከላከል እና የተለየ ሀሳብ ያላቸውን ሚዲያዎች ለማፈን የሚጠቀሙበት ሰፊ እና ግልጽ ያልሆነ ካባ ነው። ሚዲያ የህዝብ አይን እና ጆሮ እንጂ የመንግስት የፕሮፓጋንዳ ማሽን አይደለም። የሀገር ውስጥ የፀጥታ ችግሮችን ማንሳት፣ የመንግስትን ስህተት መተቸት ወይም አማራጭ ሀሳቦችን ማስተናገድ "የጠላት አጀንዳ ማስታመም" ተደርጎ የሚፈረጅ ከሆነ፣ የፕሬስ ነፃነት ህልውና ያበቃለታል ማለት ነው። ዳይሬክተሯ እንደጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ዋቢ አድርገው "ለልጁ ምን ብሎ ያወራዋል" የሚለው ስሜታዊ መከራከሪያ፣ የጋዜጠኝነትን ሙያዊ ነፃነት እና ሚዛናዊነት ከመጠበቅ ይልቅ ሚዲያው የመንግስትን ስሜት በማባበል ላይ ብቻ እንዲጠመድ የሚያስገድድ ነው።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ኃላፊዋ ሃይማኖት ዘለቀ ያቀረቡት መከራከሪያ፣ መንግስት በሚዲያዎች ላይ የሚወስደውን የማፈን እርምጃ ትክክል ለማስመሰል የተሳሳተ ዓለም አቀፍ የ"ፋክት" መረጃ ላይ የተመረኮዘ ነው። ጠንካራ ሬጉላተሪ ሲስተም (የቁጥጥር ሥርዓት) ማለት ሚዲያዎችን የሚያግድ፣ የሚያስፈራራ እና የሚያንበረክክ ሳይሆን፣ የህዝብን ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብት የሚያከብር፣ እንዲሁም ነፃ እና ገለልተኛ የፕሬስ ምኅዳርን የሚገነባ መሆን አለበት። የባለሥልጣናት ስህተት እንዳይጋለጥ በሚል የሌላን ሀገር መሪ ያልተፈፀመ ዛቻ እንደ ትክክለኛ አብነት መጥቀስ፣ ሀገሪቱ በፕሬስ ነፃነት ዙሪያ ምን ያህል ወደ ኋላ እየተጓዘች መሆኑን በግልፅ የሚያሳይ አሳሳቢ ምልክት ነው።
እጠቅሳለሁ.. "የዲሞክራሲን እና የህግን ካባ ለብሶ በ'ብሔራዊ ጥቅም' ስም እውነትን የሚያፍን አስመሳይ፣ ራሱን በግልፅ ከሚያሳይ አምባገነን የበለጠ አደገኛ ነው።"
ማርታ ከሚኒሶታ

25 days ago