(ዘ-ሐበሻ ዜና) ከትናንት በስቲያ በካርቱም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እና ሌሎች የሲቪል ተቋማት ላይ የተፈጸመውን የድሮን ጥቃት ተከትሎ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ቁጣ እያየለ መጥቷል። ኳታር ጥቃቱን ማውገዟን ተከትሎ፣ አሜሪካ ጉዳዩን ወደ ላቀ የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ማስጠንቀቂያ ደረጃ አሸጋግረዋለች። በአረብ እና አፍሪካ ጉዳዮች የአሜሪካ ከፍተኛ አማካሪ ዛሬ ባወጡት ወሳኝ መግለጫ፣ የጥቃቱ ፈጻሚዎች እና ከጀርባ ድጋፍ የሚሰጡ የውጭ ሀገራት ላይ ቀጥተኛ ጣት ተቀስሯል።
አሜሪካ በመግለጫዋ የድሮን ጥቃቱ የተፈፀመው በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሆኑን በግልፅ በማመልከት ኃይሉን በቀጥታ ተጠያቂ አድርጋለች። የሲቪል አውሮፕላን ማረፊያዎች የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቶችን እና ሰራተኞችን ለማንቀሳቀስ እጅግ ወሳኝ መሆናቸውን የጠቀሰው መግለጫው፣ እንዲህ አይነት ጥቃቶች ህይወት አድን እርዳታዎችን ለማድረስ ተጨማሪ እንቅፋት እየፈጠሩ በመሆኑ በአስቸኳይ ሊቆሙ ይገባል ብሏል።
በተጨማሪም ተፋላሚ ወገኖች ይህ አውዳሚ ግጭት ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለው አምነው እንዲቀበሉ አሜሪካ አሳስባለች። ሰብዓዊ የተኩስ አቁም ስምምነት በማድረግ፣ ወደ ቋሚ የተኩስ አቁም እንዲሸጋገሩ እና ሁሉን አሳታፊ በሆነ ሀገራዊ የውይይት መድረክ ስልጣኑን በሲቪል ለሚመራ መንግስት እንዲያስረክቡም ጥሪ አቅርባለች። የዚህ መግለጫ እጅግ ወሳኙ እና የቀጠናውን ሀገራት የሚመለከተው ነጥብ የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነትን የተመለከተው ሲሆን፣ አሜሪካ በሱዳን ግጭት ለማንኛውም ወገን የሚሰጥ የውጭ ድጋፍ ወዲያውኑ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ማብቃት አለበት በማለት አጥብቃ አስጠንቅቃለች።
ይህ የአሜሪካ መግለጫ ተራ የውግዘት ቃላት አይደለም። አሜሪካ ውጊያውን የሚያስቀጥል ማንኛውም ቀጣይነት ያለው የውጭ ድጋፍ ለግጭቱ መራዘም እና ለሱዳን ህዝብ ስቃይ ቀጥተኛ ኃላፊነት ይወስዳል ማለቷ፣ በሱዳን ጦርነት ውስጥ እጃቸው አለበት ተብለው ለሚጠረጠሩ ሀገራት የተሰጠ ቀይ መብራት ነው።
በቅርቡ ሱዳን የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች መነሻቸውን ያደረጉ ድሮኖች በኢትዮጵያ በኩል አልፈው ጥቃት እያደረሱብኝ ነው የሚል ክስ ማቅረቧ ይታወሳል። ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ይህን ብታስተባብልም፣ አሜሪካ RSFን ለድሮን ጥቃቱ ተጠያቂ ማድረጓ እና የውጭ ድጋፍ ሰጪዎችን አጥብቃ ማስጠንቀቋ የሱዳንን ክስ በተዘዋዋሪ እውቅና እንደሰጠችው ይቆጠራል። ይህም አሜሪካ ዩኤኢን ጨምሮ ሌሎች የውጭ ሀገራት ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ ጫና መፍጠር መጀመሯን ያሳያል። ይህ ክስተት በሱዳን፣ በኢትዮጵያ፣ በግብፅ እና በኤርትራ መካከል ያለውን የተወሳሰበ የጂኦ-ፖለቲካዊ ሽኩቻ ወደ አዲስ ምዕራፍ ሊያሸጋግረው ይችላል።

5 months ago