Logo
FBC
አርሰናል ከ20 ዓመታት በኋላ ለሻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ አርሰናል አትሌቲኮ ማድሪድን 1 ለ 0 አሸንፏል።

የአርሰናል ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ቡካዮ ሳካ በመጀመሪያው አጋማሽ አስቆጥሯል።

ወደ ስፔን አቅንቶ የመጀመሪያውን ዙር ጨዋታ 1 አቻ አጠናቅቆ የተመለሰው አርሰናል፥ በድምር ውጤት 2 ለ 1 በማሸነፍ ወደ ፍጻሜው አልፏል።

በዚህም አርሰናል ከ20 ዓመታት በኋላ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ተፋላሚ ሆኗል።

አርሰናል በፍጻሜው ከባየርን ሙኒክ እና ፒኤስጂ አሸናፊ ጋር ይፋለማል።

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.