በአዲስ አበባ የፕሪምየር ሊግ ደጋፊዎችን የሚያሳትፍ የብስክሌት ውድድር ሊካሄድ ነው
#ethiopia | ነፍ ኮምዩኒኬሽን እና ኤቨንት ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፣ ከቱሪዝም ኮሚሽን እና ከወጣትና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር የብስክሌት በአዲስ ወርሃዊ ፌስቲቫል አካል የሆነ ልዩ የውድድር መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን አስታውቋል።
የብስክሌት በአዲስ የፕሪምየር ሊግ ደጋፊዎች የብስክሌት ውድድር በሚል ስያሜ የተዘጋጀው ይህ መርሃ ግብር በማውንቴን እና በኮርስ ብስክሌት ዘርፎች የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ደጋፊዎችን የሚያሳትፍ ይሆናል።
ውድድሩ በሁለት ዙሮች የሚከናወን ሲሆን የመጀመሪያው ዙር የፊታችን እሁድ ግንቦት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከኡራኤል እስከ ወሎ ሰፈር በሚዘረጋው መስመር ላይ ይካሄዳል።
ሴቶች በ10 ኪሎ ሜትር እንዲሁም ወንዶች በ20 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚወዳደሩ ሲሆን አሸናፊዎች የሚለዩት በዘጠነኛው እና በአስረኛው ዙር የብስክሌት በአዲስ ፌስቲቫሎች ላይ በሚመዘገብ ድምር የሰዓት ውጤት እንደሆነ ተገልጿል።
በአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን ዳኝነት በሚመራው በዚህ ውድድር ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ለሚወጡ ተሳታፊዎች ልዩ ሽልማቶች ተዘጋጅተዋል።
በውድድሩ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ግንቦት 2 ቀን ከጠዋቱ 12 ሰዓት ከ30 ጀምሮ የሚወዳደሩበትን ብስክሌት እና የሚደግፉትን የክለብ ማልያ በመያዝ በነፃ መመዝገብ እንደሚችሉ አዘጋጆቹ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
#cycling #addisababa #premierleague #sports #cyclingevent #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

5 months ago