(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአፍሪካ ትልቁ አቪዬሽን የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በጀርመን ሀምቡርግ በተካሄደው የ2026ቱ የ 'PAX Readership' ዓለም አቀፍ የሽልማት መርሃ ግብር ላይ በአቪዬሽኑ ዘርፍ ሶስት ታላላቅ ሽልማቶችን ማሸነፉ ተገለጸ። አየር መንገዱ ዕውቅና ያገኘባቸው ሶስት ዘርፎች በአፍሪካ ምርጥ የምግብ አቅርቦት አገልግሎት ፣ በአፍሪካ ምርጥ አጠቃላይ የመንገደኞች ተሞክሮ ፣ እንዲሁም በአፍሪካ ምርጥ የህፃናት መገልገያ ቁሳቁስ የሚሉት ናቸው። እነዚህ ሽልማቶች አየር መንገዱ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የበረራ ላይ አገልግሎቶችን፣ አዳዲስ የፈጠራ ምርቶችን እና ለቤተሰብ ምቹ የሆኑ መገልገያዎችን በማቅረብ ወደር የለሽ የመንገደኞች ተሞክሮ ለመፍጠር ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳዩ መሆናቸው ተገልጿል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ሽልማቱን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት፣ በመንገደኞቻቸው እና በአቪዬሽን ዘርፍ አጋሮቻቸው ዳግም ዕውቅና በማግኘታቸው ትልቅ ክብር እንደሚሰማቸው ገልጸዋል። በሶስት ዘርፎች ማሸነፋቸውም ከበረራ ላይ ምግብ አቅርቦት አንስቶ እስከ አጠቃላይ የደንበኛ ተሞክሮ እና ለቤተሰብ ምቹ የሆኑ አገልግሎቶችን ለማሻሻል ያላቸውን የማያወላውል ትኩረት እንደሚያሳይ ተናግረዋል። አያይዘውም ይህ ስኬት ከኢትዮጵያዊ መስተንግዶ እና ከዓለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎች የተቀዳ መሆኑን፣ እንዲሁም የሰራተኛው ቡድን ታታሪነት ውጤት መሆኑን አብራርተዋል።
በዘገባው እንደተመላከተው አየር መንገዱ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን፣ የላቁ የካቢን ምርቶችን እና የበረራ ላይ የመዝናኛ ቴክኖሎጂዎችን በማቅረብ የመንገደኞችን ፍላጎት ለማሟላት እየሰራ ይገኛል። በተለይም በበረራ ላይ የሚቀርበው የህፃናት መገልገያ ቁሳቁስ ለቤተሰብ ምቹ የሆነ የጉዞ ልምድ በመፍጠር አየር መንገዱን ለሌሎች ተፎካካሪዎች አርአያ አድርጎታል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ራዕይ 2035 በተሰኘው ስትራቴጂው መሰረት ከዓለም ቀዳሚ የአቪዬሽን ግሩፖች ተርታ ለመሰለፍ እያለመ ነው። ለዚህም በኤዥያ፣ አውሮፓ እና አሜሪካ ገበያዎች ላይ ተደራሽነቱን ይበልጥ በማስፋት ዓለም አቀፋዊ ተጽዕኖውን ማሳደግ፣ ዘመናዊ እና ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ አውሮፕላኖችን በስፋት መጠቀም፣ እንዲሁም የካርቦን ልቀትን በመቀነስ በዘላቂ የአቪዬሽን ኢንደስትሪ ውስጥ ግንባር ቀደም መሆን ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫዎቹ መሆናቸው ተብራርቷል።

1 month ago