አሜሪካ ከጨረቃ በኋላ ቀጣዩ ግቧ ማርስ ነው - ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ
*****************
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአርቴሚስ 2 ተልዕኮ የጠፈርተኞች አባላትን በኋይት ሀውስ ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት፣ ከጨረቃ በኋላ ቀጣዩ ግቧችን ማርስ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በኋይት ሀውስ በተካሄደው በዚህ የዕውቅና ሥነ-ሥርዓት ላይ አራቱም የአርቴሚስ 2 ተልዕኮ አባላት የተገኙ ሲሆን፣ ፕሬዝዳንቱ ለጠፈርተኞቹ ያላቸውን ከፍተኛ አድናቆት ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለጠፈርተኞቹ ባስተላለፉት መልዕክት፤ "እናንተ የአሜሪካ እውነተኛ ጀግኖች ናችሁ" በማለት፣ ጉዟቸው የሀገሪቱን ብቻ ሳይሆን የመላው ዓለምን ትኩረት የሳበና የማይታመን ጀግንነት የታየበት መሆኑን ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ አሜሪካ በጠፈር ምርምር ያላትን መሪነት በድጋሚ ለማረጋገጥ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸው፣ በቀጣይ ጠፈርተኞችን በጨረቃ ላይ ለማሳረፍ ያለውን እቅድ አረጋግጠዋል።
"በዚህ ጊዜ ባንዲራችንን የምንተክለው ለጥቂት ጊዜ ቆይተን ለመመለስ ሳይሆን በጨረቃ ላይ ቋሚ መገኛ እንዲኖረንና ከዚያም ወደ ማርስ ለመሻገር ነው" ሲሉ የሀገራቸውን የረጅም ጊዜ የጠፈር ፍላጎት አስረድተዋል።
የአርቴሚስ 2 ጠፈርተኞች በዚህ ጉዞ እስካሁን ማንኛውም የሰው ልጅ ተጉዞ ከማያውቀው ርቀት በላይ ለ10 ቀናት ከምድር ርቀው በመጓዝ አዲስ ታሪክ ያስመዘገቡ ሲሆን፤ በጉዞው የተሰበሰበው መረጃም የሰውን ልጅ ወደ ጨረቃ ደቡባዊ ዋልታ ለሚወስደው የአርቴሚስ 3 ተልዕኮ እንደግብዓት እንደሚያገለግል ተገልጿል።
በቢታንያ ሲሳይ
#ethiopianbroadcastingcorporation #usa #artemisii #donaldtrump #spaceexploration #nasa

3 months ago