Logo
SeledaPost
የትምባሆ አብዛኛው ተጠቃሚዎች 18 ዓመት ያልሞላቸው ታዳጊዎች ናቸው ተባለ

የዓለም የጤና ደርጅት ባደረገው የዳሰሳ ጥናት መሰረት 1.3 ቢሊዮን ሰዎች  ትምባሆ ይጠቀማሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ከዚሁ ውስጥ 84 በመቶው የትምባሆ ተጠቃሚዎች በአዳጊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገታቸው በመፋጠን ደረጃ ያሉ ሀገራት ናቸው፡፡

የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የምግብና ጤና ነክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸዉ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት የትንባሆ አብዛኛው ተጠቃሚዎች 18 ዓመት ያልሞላቸው ታዳጊዎች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡በአዋጅ 11/12 2011 መሰረት ከ21 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች  ትምባሆ ሲሸጡ እና ሲጠቀሙ ከተገኙ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ይታወቃል።

ትንባሆ ማጨስ የሚያስከትላቸው ከባድ አደጋዎች እንዳሉ በህክምና ባለሙያዎች የሚገለፅ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ካንሰር፣ የልብ ህመም፣ ስትሮክ፣ የሳንባ እና የስኳር በሽታ እንዲሁም የቆዳ እርጅና ማፋጠን ዋንኛዎቹ ናቸው

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት 120 ሚሊዮን ሰዎች  ከትምባሆ መጠቀምና ተጋለጭነት ጋር ተያያዞ ለጤና ችግሮች ይጋለጣሉ፡፡

seledadotio
seledadotio
5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.