Logo
Getu Temesgen
የሉሲዎቹ ግስጋሴ
ኢትዮጵያ ኮስታሪካን ረታ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አለፈች
#ethiopia | ​በቱርክ አዘጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የ"UEFA Friendship Cup" የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ድንቅ ድል አስመዝግቧል።

ሉሲዎቹ ኮስታሪካን 1 ለ 0 በመርታት በስድስት ነጥብ ወደ ግማሽ ፍፃሜው መሸጋገራቸውን አረጋግጠዋል።

​ የጨዋታው ድምቀቶች፦

​የማሸነፊያዋ ግብ፦ ህዳአት ካሡ በ37ኛው ደቂቃ ድንቅ ግብ ከመረብ አሳርፋለች።

​የፅናት ድል፦ ምትኬ ብርሃኑ በሰማንያ ሰባተኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ብትወጣም፣ ቡድኑ በቁጥር ብልጫ ሳይበገር ውጤቱን አስከብሮ ወጥቷል።

​የአሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ ስኬት፦ በመጀመሪያው ጨዋታ ዩራጓይን 3 ለ 0 የረታው ቡድኑ፣ ዛሬም ብቃቱን አስመስክሯል።

​ ቀጣይ ትልቅ ጨዋታ

ምድባቸውን በድል ያጠናቀቁት ኢትዮጵያ እና ኖርዌይ ሚያዚያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም የምድብ አንደኝነትን ለመያዝ ይፋለማሉ።

​ሉሲዎቹ በዓለም መድረክ ኢትዮጵያን እያስጠሩ ነው!

​#getu #lucyethiopia #uefafriendshipcup #u18womensfootball #ethiopiavscostarica #challewlemecha #footballethiopia #risingstars #womeninsports #ኢትዮጵያ #ሉሲዎቹ #እግርኳስ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.