Logo
SeledaPost
እስካሁን ከ42 ሚሊዮን በላይ መራጮች ተመዝግበዋል - ምርጫ ቦርድ

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እስካሁን ከ42 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን በተመለከተ ወቅታዊ መረጃዎችን ይፋ አድርጓል።

ቦርዱ ባወጣው መረጃ መሠረት፣ እስከ ሚያዚያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በድምሩ 42,167,911 መራጮች መመዝገባቸውን ገልጿል።

ከተመዝጋቢዎቹ ውስጥ 22,746,079 የሚሆኑት ወንዶች ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ 19,421,832 ደግሞ ሴት መራጮች መሆናቸው ተመልክቷል።

ቦርዱ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ በተመለከተም 96,274 ወንድ እና 67,978 ሴት የአካል ጉዳተኛ መራጮች ለምርጫው መመዝገባቸው ታውቋል።

seledadotio
seledadotio
6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.