Logo
Getu Temesgen
የአርሰናል ለየት ያለ የልምምድ ስልት እና የነገው የሻምፒዮንስ ሊግ ፍልሚያ!
#ethiopia | የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ነገ ከስፖርቲንግ ሊዝበን ጋር ለሚያደርገው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ወሳኝ ጨዋታ ዝግጅቱን አጠናክሮ ቀጥሏል። ይሁን እንጂ መድፈኞቹ በዛሬው ዕለት ባደረጉት ልምምድ ላይ የተለየ እና ትኩረት ሳቢ ትዕይንት ተስተውሏል።

ተጫዋቾቹ በቡድን በመከፋፈል አንድን ኳስ በጭንቅላታቸው መሃል ደግፈው በመያዝ በአንድነት የመንቀሳቀስ ልምምድ አድርገዋል።
በተጨማሪም፣ በርካታ የመፃፊያ እስክሪብቶዎችን በቡድን ሆነው በጣቶቻቸው አጣምረው በመያዝ ኳስ የመግፋት እና የመቆጣጠር ያልተለመደ ልምምድ ሲሰሩ ታይተዋል።

የዚህ አዲስ የልምምድ መንገድ ዋና ዓላማ፣ ተጫዋቾቹ በሜዳ ላይ ከፍተኛ ትኩረት እንዲኖራቸው እና በአንድ ጊዜ ሁለት የተለያዩ ተግባራትን (Multitasking) በብቃት መከወን እንዲችሉ አቅማቸውን ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #አርሰናል #መድፈኞቹ #ሻምፒዮንስሊግ #ስፖርቲንግሊዝበን #እግርኳስ #ስፖርት #arsenal #championsleague #coyg

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.