Logo
YenetaTube
ባለፉት ዘጠኝ ወራት በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ከ670 ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝን ኮኬይንና ካናቢስ መያዙ ተገለፀ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ ከጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ኤርፖርት ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ጋር በመቀናጀት ከሐምሌ 2017 ዓ.ም እስከ መጋቢት 2018 ዓ.ም ባካሄደ ጥብቅ ክትትልና ፍተሻ ከ80 ኪሎ ግራም በላይ ኮኬይን እና ከ590 ኪሎ ግራም የሚመዝን አደገኛ ዕፅ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ መያዙን ገልጿል፡፡

ዓለም አቀፍ አዘዋዋሪዎቹ አደገኛ ዕፆቹን በአሳ፣ በቸኮሌት፣ በከረሜላ፣ በብስኩት፣ በዱቄት እና በተለያዩ የምግብ አይነቶች በማዘጋጀት፣ በፈሳሽ እና በሳሙና መልክ በማዘጋጀት እንዲሁም የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ሞደስ፣ አሻንጉልት እና የፀጉር ጌጣጌጥ በማስመሰል፣ በሻንጣ ላይ ሻግ በመሥራት፣ በካርቶን በማሸግ፣ በመዋጥ እንዲሁም በፀጉራቸው ውስጥ ደብቀው ለማሳለፍ ቢሞክሩም በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እና በአነፍናፊ ውሻ (K9) ታግዘው ከሚሠሩት ብቃት ካላቸው ባለሙያዎች ማምለጥ አልቻሉም።

ባለሙያዎቹ በአዘዋዋሪዎቹ የሰውነት አካል፣ በካርጎዎች እና በሻንጣዎች ላይ ባካሄዱት ጠንካራ ፍተሻ የናይጄሪያ እና የብራዚል ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎችን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ዜግነት ያላቸው 33 አደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎች ከነ-ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ሥር ማዋል ችለዋል፡፡

Ethiopian Federal Police

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.