በጣሊያን የሟች ሞዴል አስክሬን አንገት ተቀልቶ ተሰረቀ
ባለፈው ጥቅምት ወር በሚላን ከተማ በባልደረባዋ 30 ቦታ ቢላዋ ተወግታ የተገደለችው የ33 ዓመቷ ሞዴል ፓሜላ ጄኒኒ አስክሬን በድጋሚ አሰቃቂ ጥቃት ደረሰበት።
አስክሬኑ በቤርጋሞ ክልል በሚገኝ መቃብር ውስጥ ለቤተሰብ መቃብር እንዲዛወር ሲቆፈር፣ የሬሳ ሳጥኑ ተሰብሮና የሟች ጭንቅላት ተቀልቶ ተወስዶ ተገኝቷል።
ይህ በጣሊያን ከፍተኛ ድንጋጤን የፈጠረው ክስተት፣ ሌላ የ41 ዓመት ሴት ግድያ በተፈጸመ ማግስት የተሰማ ነው።
ፌዴሪካ ቶርዙሎ የተባለችው ሴት በባሏ ተገድላ አስክሬኗ ተቀብሮ ተገኝቷል።
ገዳዩ በቁጥጥር ስር ሲውል፣ ወላጆቹ በሀዘንና በውርደት ራሳቸውን አጥፍተዋል።
እነዚህ ተከታታይ አሰቃቂ ድርጊቶች በሀገሪቱ የሴቶች ጥበቃ ላይ ከፍተኛ ህዝባዊ ቁጣን ቀስቅሰዋል።
ምንጭ: ANSA

2 months ago