በጋሞ ዞን ኃይል ለተቋረጠባቸው አካባቢዎች ኃይል እንዲያገኙ እየተደረገ ነው
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአርባ ምንጭ ሪጅን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በደረሰው የተፈጥሮ አደጋ ኃይል ተቋርጦባቸው ለነበሩ አካባቢዎች ጊዜያዊ መስመር በመዘርጋት ኃይል እንዲያገኙ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡
በደረሰው የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ በአርባምንጭ ከተማ ብቻ 70 ምሰሶዎች፣ ከ4 ኪ.ሜ በላይ የመካከለኛ መስመር ውድመት እና 4 የኤ.ኤም.አይ ቆጣሪዎች በጎርፍ ተወስደዋል።
በአርባምንጭ ዙርያ በገረሴ፣ ከንባ፣ ጨንቻና ምዕራብ አባያ ወረዳዎች በድምሩ ከ150 በላይ ምሰሶዎች እንዲሁም 10 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር ውድመት ደርሷል፡፡
በተጨማሪም በአርባ ምንጭ ከተማ ቁጥር አንድ ማዕከል ግምጃ ቤት አዲስ ኃይል ጠያቂ ደንበኞችን ተጠቃሚ ለማድረግ የተቀመጡ 155 ምሰሶዎች በጎርፍ ተወስደዋል፡፡
የአርባ ምንጭ ሪጅን የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት የቴክኒክ ሠራተኞችና የሪጅኑ ሰራተኞች በመረባረብ የመልሶ ግንባታ ስራዎችን እያከናወኑ ይገኛሉ።
ሪጅኑ በዞኑ አደጋው በደረሰባቸው አካባቢዎች ለነበሩ የጤና ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች፣ የመስተዳድር ቢሮዎች እና ሌሎችም ቁልፍ ደንበኞች ኃይል ለመስጠት ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ነው፡፡
ቤታቸው በጎርፍ ከተወሰደባቸው ደንበኞች ውጪ ያሉት የአርባምንጭ፣ የገረሴ፣ የከንባ፣ የጨንቻና የምዕራብ አባያ ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው የመሬት መንሸራተት እና የጎርፍ አደጋ የሰው ህይወት ህልፈትና ንብረት ውድመት መድረሱ ይታወሳል፡፡
Ethiopian Electric Utility

7 months ago