Logo
FIDEL POST NEWS
የፌስቡክ እና ኢንስታግራም ባለቤት ሜታ ያለ ዲግሪ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ ስራ ሊቀጥር ነው

​ ሜታ በቴክኖሎጂ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዘርፎች ለሚወጡ የስራ መደቦች የዩኒቨርሲቲ ዲግሪን እንደ ግዴታ መጠቀም ማቆሙን አስታወቋል።

ኩባንያው ከአካዳሚክ ማስረጃ ይልቅ ለተግባራዊ ልምድ፣ ለግል ፕሮጀክቶች እና ለፈጠራ ችሎታ ቅድሚያ እንደሚሰጥ ገልጿል።

​እንደ ማርክ ዙከርበርግ ገለጻ፣ ወቅታዊው የትምህርት ስርአት ከቴክኖሎጂ ገበያው ፍጥነት ጋር የማይጣጣም በመሆኑ ይህ ውሳኔ ተላልፏል።

አመልካቾች በኢንጂነሪንግ እና በማሽን ለርኒንግ ዘርፎች ያላቸውን ብቃት በተግባር ማሳየት እስከቻሉ ድረስ ያለ ዲግሪ መቀጠር ይችላሉ።

​እንዴት ማመልከት ይቻላል?
​በ metacareers.com በመግባት "AI" ወይም "Software Engineering" ብሎ መፈለግ።

​በስራ ዝርዝሩ ውስጥ "Equivalent practical experience" የሚል አማራጭ መኖሩን ማረጋገጥ።

​የሰራችኋቸውን የAI ፕሮጀክቶች ወይም የኮዲንግ ስራዎች (GitHub) ማስረጃ አድርጎ ማያያዝ።

​የግል መረጃንና ሲቪን (Resume) በመሙላት ማመልከቻውን ማጠናቀቅ።

​ይህ አሰራር በራስ ጥረት የሚገኝ እውቀትን የሚያበረታታ ሲሆን፣ በተለይ ዲግሪ ለሌላቸው ባለሙያዎች ትልቅ እድል ይከፍታል ተብሏል።
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.