Logo
SeledaPost
በአፋር ክልል በደረሰ ከባድ የንፋስና የዝናብ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ።

​በአፋር ክልል ፋንቲ ረሱ ዞን ጎሊና ወረዳ ትላንት ማምሻውን በጣለ ከባድ ዝናብና ንፋስ ከፍተኛ የንብረት ውድመት ደርሷል።

​በደረሰው አደጋ በግል መኖሪያ ቤቶችና በመንግስት የልማት ተቋማት ህንፃዎች ላይ ውድመት ደርሷል። በእንስሳት፣ በእርሻ ቦታዎችና በተለያዩ የልማት ተቋማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ተመዝግቧል።

​የጎሊና ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት እንደገለጸው፤ በአደጋው ከፍተኛ የንብረት ጉዳት ቢደርስም እስካሁን ባለው መረጃ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።

seledadotio
seledadotio
3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.