ዛሬ ዓለም አቀፍ የዳውን ሲንድሮም ቀን ይከበራል
በአለም ላይ ከ650 አዲስ የተወለዱ ሕፃናት መካከል አንዱ በዚህ ሲንድሮም ይወለዳል። የዳውን ሲንድሮም ቀን መለያ ምልክት ቀለማት ያሏቸው ካልሲዎች ናቸው።
ዛሬ ስለ ዳውን ሲንድሮም (Down Syndrome) የዘረመል ልዩነትና በሰዎች ሕይወት ላይ ስላለው ተጽዕኖ ግንባዛ ለማስጨበጥ የሚውል ዓለም አቀፍ ቀን ነው።
ይህ ቀን ከፈረንጆቹ 2006 ዓ.ም ጀምሮ መከበር የጀመረ ሲሆን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረውም በሲንጋፖር ነበር።
ሲንድሮም የሚለው ስያሜ የተለመዱ ምልክቶችና ባህሪያት ስብስብ መጠሪያ ነው። "ዳውን" የሚለው ስያሜ ደግሞ እ.ኤ.አ በ1866 የችግሩ መንስኤ ከመገኘቱ ከ100 ዓመታት በፊት ሲንድሮሙን ለመጀመሪያ ጊዜ ለገለጹት እንግሊዛዊ ሐኪም ጆን ላንግደን ዳውን መታሰቢያነት የተሰጠ ነው።
የዳውን ሲንድሮም መንስኤ በ1959 በፈረንሳዊው የዘረመል ተመራማሪ ጀሮም ሌጄን ተገኘ። በ21ኛው የክሮሞዞም ጥንድ ላይ ሁለት መሆን ሲገባቸው አንድ ተጨማሪ ክሮሞዞም ተገኝቷል፤ ይህም በጠቅላላው የሴል ክሮሞዞም ብዛት 46 መሆን ሲገባው ወደ 47 ከፍ እንዲል አድርጎታል።
ክሮሞዞሞች በሰውነታችን ሴል ውስጥ የሚገኙ፣ ሁሉንም የውርስ ባህሪያት የሚሸከሙ ጥቃቅን የፕሮቲን ስብስቦች ናቸው። እያንዳንዱ ጥንድ ክሮሞዞም አንዱ ከእናት አንዱ ከአባት የሚመጣ ነው።
ዳውን ሲንድሮም ያለባቸው ሰዎች ለሚኖሩበት ማህበረሰብ የሚያበረክቱት ብዙ ነገር አላቸው። የእነሱ ልዩ ማንነት ለሚያውቋቸው ሰዎች ሁሉ አነቃቂ ነው። ሆኖም ግን፣ በግንዛቤ ማነስና ባለመቀበል ምክንያት እነዚህ ሰዎች ብዙ ጊዜ ለቅድመ-ፍርድና ለክፍፍል ይጋለጣሉ።
ስለሆነም ሁላችንም ግንዛቤ እንዲኖረንና እነዚህን ወገኖች ለመቀበል ጥረት ማድረጋችን በጣም አስፈላጊ ነው። ስለ ልዩ ፍላጎቶቻቸው ራሳችንን በማስተማር፣ ሙሉ አቅማቸውን እንዲያሳድጉና በማህበረሰቡ ውስጥ ሙሉ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማድረግ ይገባናል።
ቀለማት ያሏቸው ካልሲዎች የዚህ ቀን ምልክት የሆኑት ዳውን ሲንድሮም ያለባቸው ሰዎች ካልሲዎችን ማጣመር (መመሳሰል) ስለማይችሉ ነው። እነዚህን ካልሲዎች መልበስ እነዚህ ሰዎች ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ለሚያደርጉት ትግል ድጋፍን ማሳያ ነው።
ከኢንዲራ ፒንድዙ ፅሁፍ የተወሰደ

7 months ago