በሰዎች ትችት ምክንያት በፍጹም ልትቀይራቸው የማይገቡ 3 ወሳኝ ነገሮች
በሕይወታችን ውስጥ የሰዎችን አስተያየት መስማት ተገቢ ቢሆንም፣ የእነርሱ ትችት ግን ማንነታችንን ሊያጠፋው አይገባም።
የሚከተሉትን ሦስት መሠረታዊ ነገሮች በሰዎች ግፊት መቀየር የለብህም፦
1. የሕይወት ግቦች
ሌሎች ሰዎች ስላልረኩ ወይም ስላልመሰላቸው ብቻ የሕይወት ግቦችህን አታስተካክል። ይህንን ሕይወት የምትኖረው አንተ ነህ፤ ስለሆነም መኖር ያለብህ በራስህ ፍላጎት እና አንተ ትክክል ነው ብለህ በሚሰማህ መንገድ ነው። ያንተ ስኬት የሚለካው በሌሎች መመዘኛ ሳይሆን አንተ ለራስህ ባስቀመጥከው ግብ ነው።
2. ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች
አንተ ለሕይወትህ አስቀድመህ ቅድሚያ የምትሰጣቸውን ነገሮች (ቤተሰብ፣ ትምህርት፣ ስራ ወይም ጤና) ለይተህ ካስቀመጥክ፣ ሰው ስለተቸህ ብቻ አትቀይራቸው። እያንዳንዳችን የተለያየ የሕይወት ጉዞ እና ግብ ስላለን፣ ለእኛ ይበልጥ አስፈላጊ የሆነውን ነገር የመወሰን መብቱ የኛው ብቻ ነው።
3. መርሆች
በቅንነት ለምታምንባቸው እሴቶችህ እና የሞራል አቋሞችህ ፈጽሞ አትደራደር። በሰዎች ትችት ምክንያት መርሆችህን ከጣስክ፣ ውሎ አድሮ ራስህን መናቅ ትጀምራለህ። በራስህ መተማመን የሚመነጨው ለራስህ እውነት ሆነህ ስትገኝ ብቻ ነው።
📌 ምንጭ : The Minds Journal / Psychology & Personal Development Archives

7 months ago