Logo
FIDEL POST NEWS
ወንዶች ከሴቶች ጋር ለገበያ ሲወጡ ቶሎ የመሰላቸት ዝንባሌ እንዳላቸው ተጠቆመ

​አዳዲስ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ወንዶች ከትዳር አጋራቸው ወይም ከሴት ጓደኛቸው ጋር ለገበያ በሚወጡበት ወቅት ከ26 ደቂቃዎች በኋላ የመሰላቸት ስሜት እንደሚያሳዩ ተደርሶበታል።

ይህ ጥናት በብሪታንያ በሚገኘው ኢሴንቸር. በተባለ ተቋም የተካሄደ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ወንዶች ገበያ ላይ ረጅም ሰዓት ማሳለፍን እንደ አሰልቺ ተግባር እንደሚመለከቱት ገልፇል።

​በተቃራኒው ሴቶች እስከ ሁለት ሰዓት ድረስ ያለምንም መሰላቸት ምርጫቸውን ማከናወን እንደሚችሉ በጥናቱ ተመልክቷል።

ወንዶች ቶሎ ለመሰላቸታቸው እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው የሚፈልጉትን ነገር ለይተው በፍጥነት የመግዛት ዝንባሌ ስላላቸውና የሴቶች ረጅም የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ስለሚደክማቸው ነው።

​ምንጭ፦ Esentur Consumer Research
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.