Logo
FIDEL POST NEWS
​🧠 አእምሮን በ5 ሳምንት ስፖርት ለ20 ዓመታት መጠበቅ ይቻላል

​አዲስ የወጣ ሳይንሳዊ ጥናት እንደሚያመለክተው፣ አእምሮን የሚያሰሩ (Mental Exercises) ተግባራትን ለተከታታይ 5 ሳምንታት ብቻ በማድረግ ለአእምሮ መርሳት እና ለአልዛይመር በሽታ የመጋለጥ እድልን እስከ 20 ዓመታት ድረስ መቀነስ ይቻላል።

​የጥናቱ ዋና ነጥቦች፦
​የመረጃ ቅልጥፍና፦ ምስሎችን በፍጥነት የመለየትና ውሳኔ የመስጠት ልምምዶች ለአእምሮ መረሳት የመጋለጥ እድልን በ25% ይቀንሳሉ።

​አእምሮን "ማላብ"፦ ልምምዶቹ ውጤታማ የሚሆኑት አእምሮ ጠንከር ያሉና ፈታኝ የሆኑ ተግባራትን ሲያከናውን (ለምሳሌ፦ አዳዲስ ቋንቋዎችን መማር፣ ሂሳብ መስራትና የንባብ ልምድ) ነው።

​ዘላቂነት፦ ለጥቂት ሳምንታት የተደረገ ከፍተኛ የአእምሮ እንቅስቃሴ ውጤቱ እስከ 20 ዓመታት ድረስ አብሮ ሊዘልቅ እንደሚችል ተረጋግጧል።

​ባለሙያዎች እንደሚመክሩት ልክ ሰውነታችንን በስፖርት እንደምናጠናክረው ሁሉ፣ አእምሯችንንም ሁሌም አዳዲስ ነገሮችን በማስለመድ ከበሽታ መከላከል እንችላለን።

​📍 ምንጭ፦ Alzheimer's & Dementia Journal
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.