Logo
FIDEL POST NEWS
እስራኤል በሶማሊላንድ ሚስጥራዊ የጦር ሰፈር ለመገንባት ማቀዷ ተሰማ

​እስራኤል የየመኑን ሁቲዎች ለመምታትና የስለላ መረጃዎችን ለመሰብሰብ በሶማሊላንድ የጦር ሰፈር ለመገንባት እያጠናች መሆኑን ብሉምበርግ እና ሚድል ኢስት አይ ዘገቡ።

ባለፈው ሰኔ ወር የእስራኤል የደህንነት ባለስልጣናት በኤደን ባህረ ሰላጤ አቅራቢያ የሚገኙ የባህር ዳርቻዎችን ለዚሁ ተግባር መርምረዋል።

​እስራኤል ሶማሊላንድን በታህሳስ ወር እውቅና የሰጠች ሲሆን፣ ይህም የሁቲዎችን የሚሳኤል ስጋት ለመከላከል የታለመ ስትራቴጂካዊ እርምጃ እንደሆነ ይነገራል።

የሶማሊላንድ የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ቃዳር ሁሴን አብዲ ከእስራኤል ጋር የደህንነት ትብብር መኖሩን ቢያረጋግጡም፣ ስለ ጦር ሰፈሩ ግን ወደፊት የሚታይ መሆኑን ገልጸዋል።

​ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የሶማሊያ መንግስት የእስራኤልን እውቅና በመቃወም "ሉዓላዊነቴን ለመጠበቅ እርምጃ እወስዳለሁ" ሲል ዝቷል።

የሁቲዎች ጥቃት በቀይ ባህር ላይ ያለውን የንግድ ልውውጥ በ70 በመቶ ቀንሶታል።

​ምንጮች፦ Bloomberg, Middle East Eye
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.