ባለ 20 ሊትሩ የታሸገ የ“ጃር” ውሃን ጥራት ለመለካት የሚያግዝ ጥናት ሊካሄድ ነው
በተለምዶ “ጃር” እየተባለ በሚጠራውና በ20 ሊትር መያዣ ታሽጎ ለገበያ በሚቀርበው የመጠጥ ውሃ ላይ በተደጋጋሚ የሚነሱ የጥራት መጓደል ቅሬታዎችን ለመፍታት የሚያግዝ አገር አቀፍ ጥናት ሊካሄድ እንደሆነ ያስታወቀው የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ባለሥልጣን ነው።
ባለሥልጣኑ ለአሐዱ እንደገለጸው፣ ጥናቱ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት እና የሕብረተሰቡን ጤና መጠበቅን ዓላማ ያደረገ ነው።
“ከሕብረተሰብ ጤና እና ደህንነት የሚበልጥ ምንም ዓይነት ነገር የለም” ያሉት የባለሥልጣኑ የምግብ ኢንስፔክሽንና ሕግ ማስፈጸም ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙላቱ ተስፋዬ፣ ከተገልጋዮች በየጊዜው የሚደርሱ ጥቆማዎችና አቤቱታዎችን መሠረት በማድረግ ተቋሙ በጃር ውሃ ጥራት ላይ ጥብቅ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ሥራ አስፈጻሚው በማብራሪያቸው የጥራት ችግሩ የዜጎችን ጤና አደጋ ላይ የሚጥል ሆኖ ከተገኘ ምርቱ ሙሉ በሙሉ ሊታገድ እንደሚችል ጠቁመዋል።በተጨማሪም “ባለ 20 ሊትሩ የታሸገ ውሃ መያዣ (ጃሩ) ተደጋግሞ ጥቅም ላይ የሚውል በመሆኑ፣ በጽዳት እና ሥርጭት ሂደት ከፍተኛ ጥንቃቄን ይፈልጋል።” ብለዋል።
ባለሥልጣኑ በአሁኑ ወቅት ከአመራረት እስከ ገበያ ያለውን ሂደት በመከታተል እና ናሙና በመውሰድ ምርመራ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
በማከፋፈያ ቦታዎች ላይ ጭምር ክትትል እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን፤ የተፈጠረውን የጥራት ስጋት በዘላቂነት ለመፍታት የሚካሄደው አገር አቀፍ ጥናት እንደተጠናቀቀም፣ የምርቱን ደህንነት የሚያረጋግጥ አዲስ መመሪያ ይፋ ሊደረግ እንደሚችል ተጠቁሟል።
#አሐዱ

7 months ago