እምነት፣ ንግድ እና በጎ አድራጎትን ያጣመረው 3ኛው የኢትዮ ኢድ ኤክስፖ በድምቀት ተከፈተ
#ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ጊዮን ሆቴል፣ የንግድ እንቅስቃሴን ከመንፈሳዊ እሴቶችና ከባህል ጋር የሚያስተሳስረው 3ኛው ታላቁ የኢትዮ ኢድ ኤክስፖ በይፋ ተከፍቷል።
በደማቁ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ የባህልናስፖርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኢታ ነፊሳ አልማህዲ ፣ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት አማካሪ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ፣ የእስልምና ታሪክ ተመራማሪ ፕ/ር አደም አህመድ እና ሌሎች የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
በቀላል ራዕይ ተጀምሮ በአጭር ጊዜ ውስጥ ቤተሰብን፣ ወጣቶችን፣ የስራ ፈጣሪዎችን እና ምሁራንን በአንድ ጥላ ስር መሰብሰብ የቻለው ይህ ኤክስፖ፣ የዘንድሮውን ዝግጅት ከንግድ ትርዒትነቱ ባለፈ ማህበራዊና መንፈሳዊ እሴቶችን በማጉላት ለየት ብሎ ቀርቧል።
የዘንድሮው ኤክስፖ ዋና ዋና ትኩረቶች፦
* መንፈሳዊነት እና የአዛን ውድድር፡ የዘንድሮው ዝግጅት ልዩ ትኩረት የታላቁን ሶሃባ የቢላል ኢብኑ ረባህን (ረ.ዐ) የእኩልነትና የአንድነት ጥሪ የሚዘክረው የአዛን ውድድር ነው። ይህ ውድድር ወጣቶች ከጥሪው መንፈሳዊ ውበት ጋር ይበልጥ እንዲተዋወቁ ለማድረግ ያለመ ነው።
* ማህበራዊ ሃላፊነት እና በጎ አድራጎት፡ ኤክስፖው ማህበራዊ ሃላፊነትን በመወጣት በኩልም ትልቅ ርምጃ ወስዷል። ከሚናሬት ኢንጂነሪንግ ጋር በመተባበር ከቲኬት ሽያጭ፣ ከቲክቶክ ቻሌንጅ እና ከሪል እስቴት ዘርፍ ልግስና የሚሰበሰበው ገቢ አቅመ ደካሞችንና ችግረኞችን ቤት ለመገንባት እንደሚውል ተገልጿል።
በአጠቃላይ ይህ የኢትዮ ኢድ ኤክስፖ መድረክ የኢትዮጵያውያንን የመረዳዳት ባህል፣ አብሮነት እና የንግድ እድገት በማስተዋወቅ ረገድ ብሩህ ተስፋን ያሳየበት ሆኖ አልፏል።
📸 ከበደ መክብብብ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

7 months ago