Logo
FIDEL POST NEWS
"ሌሎች ለምን እንደ እኔ አያደርጉም?" — በዱባይ ጥቃት ወቅት በ100 ሺህ ፓውንድ በግል ጄት ያመለጠው ባለሀብት ትችት እየቀረበበት ነው

​ብሪታንያዊው ባለሀብት ሳሙኤል ሊድስ በዱባይ ላይ ጥቃት በተሰነዘረበት ወቅት በግል ጄት ተከራይቶ ከአገር መውጣቱን የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ ሚዲያ ካጋራ በኋላ ከፍተኛ ትችት እየተሰነዘረበት ይገኛል።

ሊድስ ለጄት ኪራይ 100,000 ፓውንድ በመክፈል ወደ ለንደን መብረሩን ገልጾ፣ "ሌሎች ሰዎች ለምን እንዲህ አያደርጉም?" ሲል መጠየቁ ብዙዎችን አስቆጥቷል።

​ተከታዮቹ "ልጆች የያዙ እናቶችን ከመርዳት ይልቅ ራስ ወዳድነት አሳይተሃል" በሚል ቢወቅሱትም፣ እርሱ ግን ለሰዎች ጥሪ አቅርቦ ፈቃደኛ እንዳልሆኑ በመጥቀስ ምላሽ ሰጥቷል።

ለጉዞው ምክንያት ያደረገው በብሪታንያ ከ1,000 በላይ ሰዎች የሚታደሙበት የቢዝነስ ፕሮግራም ስላለው እንደሆነ ገልጿል።

ሊድስ አክሎም የዱባይ ደህንነት አስተማማኝ መሆኑንና ሚዲያዎች የሚያቀርቡትን የተጋነነ ዘገባ ህዝቡ እንዳያምን አሳስቧል።
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.