Logo
Getu Temesgen
The Magic Man ሊዮኔል ሜሲ በነጩ ቤት ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ...

በኤፍሬም የማነ
#ethiopia | ሜሲ አንተ ታላቅ ኮኮብ ነህ ። አሜሪካን መርጠህ የአሜሪካን እግር ኳስ በማነቃቃትህ እንከብርሃለን ። አንተ እና ክርስትያኖ ሮናልዶ ድንቅ ስፖርተኞች ናችሁ ። የእኔ የምንግዜውም ምርጥ ፔሌ ነው ። ፔሌ ታላቅ ተጨዋች ነው ። ከፔሌ እና ከሜሲ ማን ይበልጣል ? ሰውየው በአዳራሹ የተሰበሰው ሰውን ሁሉ ጠየቁ ? ሁሉም ሜሲ አለ ? ዶናልድ ትራምፕ ቀጠሉ ። አዎ ይሄ ሰው ሳይበልጥ አይቀርም ። ፔሌ ድንቅ ነው ። ሜሲ ግን የምንግዜውም ምርጥ ነው ። በዚህ ሀሳብ እኔም እስማማለሁ ። ሜሲ የአሜሪካ እግር ኳስን እስከወዲኛው በመቀየርህ በድጋሜ እናመሰግናለን ። ይሄ ሰው የአለም ሻምፒዮን ነው ። ይሄ ሰው 47 የተለያዩ ታላላቅ ዋንጫዎችን በእግር ኳስ ያሸነፈ ተዓምረኛ ነው ። ሊዮ አንተ ታላቅ ተጨዋች ነህ ። በርካቶችን በዚህ ጥያቄ ማስማማት ችልሃል ። ይህ የአሜሪካው ፔሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በነጩ ቤት ኦቫል ኦፊሳቸው አርጀንቲናዊ ጥበበኛ ሊዮኔል ሜሲና የMLS ሻምፒዮኖቹን በተቀበሉት ዝግጅት የተናገሩት ነው ።

ዘመናዊው እግር ኳስ ባለፉት 20 ዓመታት ለውበት ሞናሊዛዋ አርጀንቲናዊ ክብር እንደሰገደች ዛሬም አለች ። ከሮዛሪዮ ሳንታፌ ተነስቶ በምትሃቱ ዓለምን የወረረው ሊዮኔል ሜሲ በባርሴሎና በከፍታው ጥግ አንፀባርቆ በፔዤ አድርጎ የዓለም እግር ኳስ ዋንጫን ከኳታር ሉሱያል ከህሊና መቼም ከማይጠፋ ተዓምሩ ጋር ድል ነስቶ በኢንተር ሚያሚ ደምቆ ዛሬም አለ ። The Magic Man ሊዮኔል ሜሲ በመጨረሻም ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የMLS ዋንጫን ከሚያሚ ጋር አሸንፎ በWhite house ተገናኝቷል ። ጥያቄው በዚህ ፕሮግራም ለምን የኢንተር ሚያሚው ባለቤት የእንግሊዙ ኮኮብ ዴቭዴ ቤካም ያልተገኘው የሚለው ሆኗል ። እንደ የተለያዩ ዘገባዎች ቤክስ British Poster Boy በፓሪስ ፈረንሳይ የባለቤቱ
ቪክቶሪያ አንድ የፋሽን ዓለም አቀፍ ዝግጅት ላይ ለመታደም ሲል እንደቀረ ተዘግባል ።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.