ትናንት የሜትር ታክሴ ተጠቅሜ ነበር። ባለቤቱ/ሹፌሩ ወጣት ነው። ተሽከርካሪዋ በስራ ብዛት፣ እራሱን፣ ቤተሰቡንና ተናጣቂዋን በመቀለብ የደቀቀች "ቪትዝ" ነች።
እንደተለመደው ስራ እንዴት ነው ብዪ የውይይት ርዕስ ከፈትኩ።
"ስራስ አልጠፋም ነበር። የትና እንዴት ስራውን እንስራ ነው ችግሩ" አለኝ እርስ በርሱ የሚጋጭ ሐሳብ ስለሆነብኝ እንዲያስረዳኝ ጠየቅኩት ..
"መቆም፣ መንቀሳቀስና መላወስ ችግር ሆኗል። የትራፊክ ሕጉ በሌለ መንገድ፣ በሌለ የትራፊክ ምልክትና በየእለቱ በሚለዋወጥ መመርያ፣ ክልከላ፣ መንገድ የመዘጋት ውጥንቅጥና በወኋ ቀጠነ የሚያስከስስ ነው።"
"እንጀራህን ለማሸነፍ ቁጣውን ችለህ አንገትህን ደፍተህ ለመቀጣት ስትዘጋጅ ደግሞ ነጥብ ተይዟል በሚል በቅጣት ላይ ቅጣት እየተደራረበብህ ሰርተህ መብላት የማትችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው" አለኝ። ቀጠል አደረገና
"አንድ ሰው ባንድ ጥፋት እንዴት ሁለቴ ሶስቴ ይቀጣል። እውነቱን ልንገርህ ከፍቶኛል፣ ልጅ ባይኖረኝ ኖሮ መኪናዪን ሸጬ እስደድ ነበር አለኝ።"
ላረጋጋው ሞከርኩ። ዓይኑን እያበሰ ቀጠለ።
"እኛስ ዜጎች አይደለንም ? ጥገኛ ከመሆን ወንጀለኛ ከመሆን፣ ሰርተን እንብላ ነው ያለነው ? ምን አጠፋን? የሚያየን፣ ችግራችንን የሚረዳና የሚሰማን እንዴት እናጣለን ? ጎዳና ብንወጣ ቤተሰብ፣ ሀገርና መንገስት አይጎዳም ? ጠየቀኝ
"እየተብሰከሰ ምሬቱን ቀጠለ ...
"ውጤት ሳይመጣለት ቀርቶ ቤተሰቦቹ በገዙለት ተሽከርካሪ የሜትር ታክሲ ስራ እንደጀመረና በአንድ ወቅት ስራው ጥሩ ስለነበር ቤተሰብ እንደመሰረተ ገለጸልኝ" በመቀጠልም
"በኑሮ ውድነት ላይ ልጅ ይዞ ስራውን ማስቀጠል እያዳገተው እንደሆነና ጎማ መግዛት ተሽከርካሪውን ማደስ እንዳቃተው በዚህ ከቀጠለ ደግሞ አንድ ቀን ተሽከርካሪው ተንገጫግጮ እንደሚቆምና አማራጭ ስለሌለው ቤተሰቡን ጥሎ ሊሰደድ ወይም ራሱን ሊያጠፋ እንደሚችል ገለጸልኝ።"
"ታውቃለህ በዚህ ሳምንት ብቻ ሶስቴ ተቀጥቻለሁ። ነጥብ ተይዞብሃል በሚል ከዋነኛ ቅጣቱ ጋር ተደማምሮ 5000 ሺህ ብር እንደከፈለና ትርፉን በሙሉ ለቅጣት እንዳስረከበ ባለፈው ዓመትም 55 ሺህ ብር (በወር 5000) ግብር በመክፈሉ ለክፉ ቀን ለጥሪት ብሎ የያዘውን ገንዘብ እንዳሟጠጠ አክሎ ነገረኝ።
ብሶቱ፣ ምሬቱና መብሰክሰኩ አንጀት ድረስ ዘልቆ የሚሰማና የሚያቅለሸልሽ የሕመም ስሜት የሚለቅብህ የመጠቃት ስሜት ነው። የሚያወራው መድረሻ በማጣት መንፈስ እንባ እየተናነቀው ነው። ነገስ ማን ይቀጣኛል ? በሚል ስጋት ተሸማቅቄ መድረሻ እያጣሁ ነው።" አለኝ በድጋሚ አይዞህ ብዪ ለማጽናናት ሞከርኩ። ምን ያህል እንደተሳካልኝ ሳላውቅ የቀጠሮ ቦታዪ ስለደረሰ ወረድኩ።
በየስራ ዘርፉ ይህ ገጠመኝ የብዙ ወጣቶች መራራ የሕይወት ፈተና ነው። ውጤት አምጥቶ ተምሮ ስራ ማግኘት፣ በአነስተኛና ጥቃቅን ተደራጅቶ መስራት ተረት በሆነበት፣ ራቅ ብሎ ሔዶ እንደነገሩም ቢሆን ትንሽ ስራ ሰርቶ ማደገና መለወጥ በማይታሰብብት ጊዜ የተገኘው ስራ ሰርቶ በሕይወት ለመቆየት እንዳይቻል አቅምን የሚፈታተነው ሕጋዊም ሆነ ሕግ የማያውቀው ወጭና አምጣና ተቀጣ የትየለሌ ነው።
በሜትር ታክሲ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ከመንግስትና ከቤተሰብ ጥገኝነት እራሳቸውን አላቀው፣ ከወንጀል ርቀው ሕይወትን ለማሸነፍ እየታገሉ ነው። በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከ300 ሺ የማይተናነስ ወጣት በዚህ ስራ ላይ ተሰማርቷል። እነዚህ ዜጎች ግዴታ እንዳለባቸው ሁላ ሰርተው የመብላት መብታቸው ሊከበርላቸውና ሊረጋገጥላቸው ይገባል።
ከመንግስት፣ ከሕዝብና ከቤተሰብ ጫንቃ ላይ ወርደው እራሳቸውን ለመቻል ሲፍጨረጨሩ፣ ስራቸውን ለማከናወን የሚያስችላቸው አመቺ ሁኔታ መፈጠር፣ መበረታታትና መታገዝ አለባቸው። በራሳቸው ጥረት እዚህ ከደረሱ መንግስት ብሶታቸውን ሊያዳምጥና መፍትሔ ሊፈለግላቸው ይገባል።
የት ቦታ ቆመው፣ ተሳፋሪ ጭነው፣ አውረደውና ተሳፋሪ ጠብቀው መስራት እንደሚችሉ ስርዓት ሊበጅላቸው ይገባል። ቀኑን ሙለ የሚያሽከረክር አሽከርካሪ አይደለም ለአጭር ጊዜ የሚንቀሳቀስው አሽከርካሪ ደንብ ሊተላለፍ የሚችልበት እድልና አጋጣሚ በርካታ ነው።
ሕግ ማክበር እንደተጠበቀ ሆኖ በአንድ ጥፋት ተደራራቢ ቅጣት በመቅጣት አማራጭ በማሳጣት፣ ከአቅም በላይ በሆነ የግብር ጫና ዜጎችን ተስፋ ማስቆረጥ፣ አቅማቸውን ማራቆትና ሞራላቸውን መስበር አሁንም ደግሞ ደጋግሞ ሊታሰብበት የሚገባ ነው።
ጆሮ ያለው ይስማ፤ ልብ ያለው ልብ ይበል !!
የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ሙሼ ሰሙ

7 months ago