Logo
FIDEL POST NEWS
በልጅነት የፍቅር እጥረት ያጋጠማቸው ሰዎች የሚያሳዩዋቸው 5 ባሕርያት

​​የቤተሰብ ፍቅር በታጣበት ወይንም ቀዝቃዛ በሆነ አካባቢ ያደጉ ሰዎች ፍቅርን ለመረዳት፣ ለመግለጽም ሆነ ለመቀበል ይቸገራሉ።

እንዲህ ዓይነት ተሞክሮዎች በጓደኝነትም ሆነ በፍቅር ግንኙነቶች ላይ ተጽዕኖ የሚያሳርፉ አምስት ዋና ዋና ባሕርያትን ያስከትላሉ፦

​1. ሰዎችን ለማስቀረብ መቸገር

​እነዚህ ሰዎች በዙሪያቸው ጠንካራ የመከላከያ ግንብ ይገነባሉ። ይህ ግንብ ሊደርስባቸው ከሚችል የስነ-ልቦና ሕመም እና ተስፋ መቁረጥ ይጠብቃቸዋል። በዚህም ምክንያት ከልክ ያለፈ የራስ-በራስ መተማመን ያዳብራሉ፤ ስሜታቸውንም ብቻቸውን መጋፈጥ ይመርጣሉ።

​2. ግልጽ ለመሆን መፍራት

​ስሜት በግልጽ በማይገለጽበት ቤት ውስጥ ያደገ ልጅ፣ ስሜቱን ማሳየት እንደ ድክመት ወይም እንደ አደጋ ሊቆጥረው ይችላል።

ባለሙያዎች እንደሚመክሩት፣ እምነት በሚጣልባቸው ግንኙነቶች ውስጥ ቀስ በቀስ ስሜትን መግለጽ መለማመድ ለውጥ ያመጣል።

​3. ስሜትን የመረዳት ችግር

​ስሜቶች በግልጽ በማይወሩበት ቤት ውስጥ የሚያድጉ ልጆች፣ የራሳቸውንም ሆነ የሌሎችን ስሜት ለይተው ለማወቅ ይቸገራሉ።

ይህ ብዙውን ጊዜ ከወላጆች ወደ ልጅ የሚተላለፍ የትውልድ ጠባሳ ውጤት ሊሆን ይችላል።

​4. ዝቅተኛ በራስ መተማመን

​ከወላጆች በቂ ስሜታዊ ድጋፍ እና እውቅና አግኝቶ ያላደገ ልጅ፣ ራሱን እንደ ዋጋ ቢስ አድርጎ ሊቆጥር ይችላል። ይህ በልጅነት የተፈጠረ ስሜት እስከ አዋቂነት ዘመን ድረስ አብሮ በመጓዝ የብቸኝነት ስሜትን ይጨምራል።

​5. እምነት ማጣት

​በልጅነት በቂ ስሜታዊ ትስስር ያላገኙ ሰዎች፣ አዋቂ ሲሆኑ ሌሎችን ለማመን ይቸገራሉ። በቤታቸው ያጋጠሟቸው መጥፎ ተሞክሮዎች "ሌሎች ሰዎች ይጎዱኛል" የሚል ስጋት እንዲያሳድሩ ያደርጋቸዋል።

ባለሙያዎች እንደሚጠቁሙት፣ እነዚህን ስሜታዊ አደጋዎች ቀስ በቀስ በመጋፈጥ እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እምነትን በመገንባት ጤናማ ግንኙነት መፍጠር ይቻላል።

ምንጭ፦ YourTango
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.