የአሜሪካው ኤፍ-15 የጦር ጀት በኩዌት ተከሰከሰ
ዛሬ ሰኞ የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም አንድ የአሜሪካ አየር ኃይል ንብረት የሆነ F-15E Strike Eagle የጦር ጀት በምዕራብ ኩዌት መከሰከሱ ተሰምቷል።
እንደ መጀመሪያ መረጃዎች ገለጻ፣ የጦር ጀቱ አብራሪ አውሮፕላኑ መሬት ከመመታቱ በፊት በፓራሹት ለቆ በመውጣቱ ለጥቂት ከሞት ተርፏል።
በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚዘዋወሩ ምስሎች እንደሚያሳዩት፣ ፓይለቱ በአካባቢው በነበሩ የኩዌት ሲቪሎች እርዳታ ተደርጎለት ቀላል ጉዳት የደረሰበት ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሆስፒታል የሕክምና ክትትል እየተደረገለት ይገኛል።
የአደጋው መንስኤ እስካሁን በይፋ ባይታወቅም፣ አውሮፕላኑ በቴክኒክ ብልሽት ወይም በስህተት በተተኮሰ የፀረ-አውሮፕላን ሚሳይል ሳይመታ እንዳልቀረ ግምቶች እየተሰጡ ነው።
የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (CENTCOM) በአደጋው ዙሪያ ዝርዝር ምርመራ መጀመሩን የገለጸ ሲሆን በቀጣይ ይፋዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።
ይህ ክስተት የተከሰተው በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ቀጠናዊ ውጥረት በከፍተኛ ሁኔታ በጨመረበት ወቅት መሆኑ ጉዳዩን ዓለም አቀፍ ትኩረት እንዲያገኝ አድርጎታል።
seledadotio

7 months ago