Logo
FIDEL POST NEWS
የኢራቅ የታጠቀ ቡድን ካታኢብ ሄዝቦላህ
በአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃት እንደሚያደርስ አስጠነቀቀ

​የኢራቁ ተደማጭነት ያለውና በኢራን የሚደገፈው ካታኢብ ሄዝቦላህ በአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር መዘጋጀቱን አስታወቀ።

ቡድኑ ይህንን ማስጠንቀቂያ የሰጠው ዛሬ በደቡብ ኢራቅ በሚገኘው የጁርፍ አል-ሳካር የጦር ሰፈር ላይ የተፈጸመውን የአየር ጥቃት ተከትሎ ነው።

​በተሰነዘረው ጥቃት ቢያንስ ሁለት የቡድኑ ተዋጊዎች መገደላቸውንና ሌሎች አምስት መቁሰላቸውን የድርጅቱ ምንጮች አረጋግጠዋል።

የቡድኑ መግለጫ "ለተፈጸመብን ጥቃት ምላሽ ለመስጠት በቅርቡ በአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃት መጀመራችን አይቀሬ ነው" ሲል ዝቷል ማለቱን TASS ዘግቧል።

​በተያያዘ ዜና ሉፍታንሳ ወደ እስራኤልና መካከለኛው ምስራቅ የሚያደርጋቸውን በረራዎች በሙሉ እስከ መጋቢት ወር መጀመሪያ ድረስ ሰርዟል። ሁኔታው ወደ ሰፋ ያለ ቀጠናዊ ጦርነት ሊያመራ እንደሚችል ተሰግቷል።
8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.