Logo
Getu Temesgen
በትግራይ እና አማራ ክልሎች መካከል የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው የምርጫ ክልሎች የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ አሳለፈ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ምክር ቤቱ በአማራና በትግራይ ክልሎች መካከል አከራካሪ በሆኑ አምስት የምርጫ ክልሎች ላይ ልዩ ውሳኔ ማሳለፉን አሳውቋል።

ምክር ቤቱ ለቦርዱ በላከው ደብዳቤ በሚገልጸው መሰረት፦
-ሁመራ፣
-አዲረመፅ፣
-ኮረም አፍላ፣
-ጠለምት እና
-ራያ አላማጣ የይገባኛል ጥያቄያቸው እልባት እስኪያገኙ ድረስ ከትግራይ ክልል ውጭ ሆነው እንዲቆዩ መወሰኑን ይገልጻል።

በውሳኔው መሰረት አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ድምፃቸውን የሚሰጡት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይም ለፌዴራል ብቻ ነው።

እንዲሁም፣ በእነዚህ ቦታዎች ያለው "የይገባኛል" ጥያቄ፣ በህገ-መንግስታዊ ስርዓት መፍትሄ እስኪያገኝ ድረስ፣ የክልል ምክር ቤት ምርጫ ለጊዜው ተራዝሞ ወደፊት እንዲካሄድ ተወስኗል።

ምርጫ ቦርድ በበኩሉ፣ የፌዴሬሽን ም/ቤቱን ውሳኔ ተፈጻሚ ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አሳውቋል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #thiqah #tigray #amhara #neb

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.