በሚላኖ የኦሊምፒክ መንደር የኮንዶም እጥረት አጋጠመ
#fastmereja I በሚላኖ ኮርቲና የክረምት ኦሊምፒክ ላይ የሚሳተፉ ስፖርተኞች የቫለንታይን (የፍቅረኛሞች) ቀንን በታላቅ የኦሊምፒክ ስሜት የተቀበሉት ይመስላል፤ በዝግጅቱ ላይ በነፃ እንዲታደሉ የተዘጋጁ ኮንዶሞች ገና ቀኑ ሳይደርስ ተሟጥጠው ማለቃቸው ተነግሯል።
የውድድሩ አዘጋጆች በከተማው እና በተራራማው አካባቢ በሚገኙ የስፖርተኞች ማረፊያ መንደሮች 10,000 የሚጠጉ ኮንዶሞችን አሰራጭተው ነበር። ይህ በኦሊምፒክ ታሪክ የተለመደ አሰራር ሲሆን፣ ዓላማውም በቅርብ ርቀት አብረው በሚኖሩ ወጣት እና ብርቱ ስፖርተኞች መካከል ደህንነቱ የተጠበቀ ግንኙነት እንዲኖር ማበረታታት ነው።
ውድድሩ ሊጠናቀቅ ከአንድ ሳምንት በላይ እየቀረው ቅዳሜ ዕለት ክምችቱ ሙሉ በሙሉ አልቋል። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ቃል አቀባይ ማርክ አዳምስ በቀልድ መልክ እንደገለጹት፤ "ይህ የሚያሳየው የቫለንታይን ቀን በመንደሩ ውስጥ በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ መሆኑን ነው። 10,000 ኮንዶሞች ለ2,800 ስፖርተኞች ታድለዋል፤ እንግዲህ ቀሪውን ስሌት ለእናንተ እተዋለሁ።"
አዘጋጆቹ ፍላጎቱ ካሰቡት በላይ መሆኑን አምነው፣ እስከ ሰኞ ድረስ ተጨማሪ አቅርቦቶች እንደሚመጡና እስከ ውድድሩ ፍፃሜ ድረስ በየቀኑ እንደሚሞሉ አስታውቀዋል።
የኮንዶሞቹ በድንገት ማለቅ ራሳቸውንም ስፖርተኞቹን አስገርሟቸዋል። "ዛሬ ጠዋት ሳይ ደነገጥኩ፤ እንደ ሁሉም ሰው እኔም ግርም ብሎኛል" — ዶኖቫን ካሪሎ (የሜክሲኮ የበረዶ ላይ ተንሸራታች)
የማዳጋስካር ተወካይ የሆነችው ሚያሊቲያና ክሌርክ ደግሞ በእያንዳንዱ ህንፃ መግቢያ ላይ የነበሩ ሳጥኖች በየቀኑ ባዶ መሆናቸውን ገልጻለች። አንዳንዶች ኮንዶሙን ለጓደኞቻቸው እንደ ስጦታ (Souvenir) እንደሚሰጡም ጠቁማለች።

8 months ago