በሉቭር ሙዚየም የ10 ሚሊዮን ዩሮ የማጭበርበር ወንጀል ተደረሰበት!
በፈረንሳይ ፓሪስ የሚገኘውና በዓለም ላይ በብዛት ሰው የሚጎበኘው የሉቭር (Louvre) ሙዚየም፣ በከፍተኛ የቲኬት ማጭበርበር ወንጀል ሳቢያ አዲስ ቀውስ ውስጥ ገብቷል።
💰 የገንዘብ መጠኑ፦ እስከ 10 ሚሊዮን ዩሮ የሚገመት ዝርፊያ ተፈጽሟል።
⚖️ የተያዙ ሰዎች፦ የሙዚየሙ ሁለት ሰራተኞች እና አስጎብኚዎችን ጨምሮ 9 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
🔍 የተንኮል ሴራው፦ አስጎብኚዎች ለቻይናውያን ጎብኚዎች የቆረጡትን አንድ ቲኬት ለብዙ ሰዎች ደጋግመው በመጠቀም እና ለሙዚየሙ ሰራተኞች ጉቦ በመስጠት ቁጥጥርን ሲያልፉ እንደነበር ተደርሶበታል። ይህ ድርጊት ላለፉት 10 ዓመታት ሳይታወቅ ሳይቀጥል እንዳልቀረም ይታመናል።
🏢 የሀብት ምንጭ፦ የተገኘው ህገ-ወጥ ገንዘብ በሪል እስቴት ላይ ኢንቨስት ሲደረግ እንደነበር የተጠረጠረ ሲሆን፣ ፖሊስ ወደ 1.5 ሚሊዮን ዩሮ የሚጠጋ ጥሬ ገንዘብና በባንክ ያለ ሒሳብ አግዷል።
ከዚህ በፊት ምን ተከስቶ ነበር?
ይህ የቲኬት ማጭበርበር የተሰማው፣ ሙዚየሙ ባለፈው ጥቅምት ወር የደረሰበትን የ88 ሚሊዮን ዩሮ የጌጣጌጥ ስርቆት ገና ሳይረሳ ነው። በወቅቱ ዘራፊዎች በ7 ደቂቃ ውስጥ የፈረንሳይ የንግሥና ጌጣጌጦችን ይዘው በሞተር ሳይክል አምልጠው ነበር።
የሙዚየሙ አስተዳደር "ከፍተኛ የማጭበርበር መረብ መኖሩን እንጠረጥራለን" በማለት ለፖሊስ ጥቆማ መስጠቱን አስታውቋል።

8 months ago