የሙያ ፈቃድ‼️
የጤና ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ ባወጡበት መስራታቸውን የሚገልፅ ስራ ልምድና አስፈላጊውን መስፈርት ካሟሉ በሰለጠኑበት ሙያ ሁሉ የሙያ ፈቃድ ሊያድሱ የሚችሉበት ሁኔታ መኖሩን ተመላከተ፡፡-
የጤና ባለሙያዎች ምዝገባ እና የሙያ ስራ ፈቃድ አሰጣጥ አስተዳደርና ቁጥጥር መመሪያ 770/2013 ስለ ጤና ባለሙያ የሚያስቀምጣቸው ነጥቦች ·
.አንድ ባለሙያ የትምህርት ዝግጅቱ የተለያየ ሆኖ የሙያ ፍቃዱን በማውጣት በሙያ ፈቃዱ እየሰራበት መሆኑን የሚገልፅ የስራ ልምድ የሚያቀርብ ከሆነ በሰለጠነበት ሙያ ሁሉ ሙያ ፈቃድ ማውጣት የሚችልባቸው ሁኔታዎች መኖራቸውን ፡፡·
. አንድ ባለሙያ በሰለጠነበት ሙያ ሁሉ የሙያ ፍቃዱን ለማደስ ግን በሙያ ፈቃዱ እየሰራበት መሆኑን የሚያሳይ የስራ ልምድ የሚያስፈልግ መሆኑንና ለሁሉም ት/ት ዝግጅት የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችል ከሆነ እና የተማረው ሙያ ደግሞ የተለያዩ የሙያ መስኮች ከሆነ የሙያ ፍቃድ ማደስ የሚችልባቸው ሁኔታዎች መኖሩን ይገልጻል ፡፡·
በሁለት ሙያ የሙያ ስራ ፈቃድ ስለማውጣትና የስራ ልምድ አያያዝ በተመለከተ
በክሊኒካል መስክ እየሰራ ያለ ባለሙያ MPH ቢማር በሁለቱም ሙያ ፈቃድ ማውጣት ይችላል።
ጠቅላላ ሐኪም (GP) የነበረና MPH የተማረ ባለሙያ ፐብሊክ ሄልዝ ስፔሻሊስት የሚለውን ጨምሮ ለሁለቱም ሙያዎች ፈቃድ ማውጣት ይችላል፤
የዲፕሎማ ነርስ ሆኖ ቆይቶ በጤና መኮንንነት (HO) ዲግሪ አግኝቶ የብቃት ምዘና ያለፈ ባለሙያ መምረጥ የሚችለው አንዱን ፈቃድ ብቻ ነው።
ዲፕሎማውን ከመረጠ ለዲግሪ ትምህርት ያሳለፈው ጊዜ እንደ ስራ ልምድ ይያዝለታል።
የጤና መኮንን (HO) የነበረና ህክምና (MD) ተምሮ የብቃት ምዘና ያለፈ ባለሙያ መምረጥ የሚችለው አንዱን ፈቃድ ብቻ ነው። የጤና መኮንንነቱን ከመረጠ ለህክምና ትምህርት ያሳለፈው ጊዜ እንደ ስራ ልምድ ይያዝለታል።
የስራ ልምድን በተመለከተ ተዛማጅ ለሆኑ ሙያዎች ባለሙያው በትምህርት ላይ የቆየበት ጊዜ ለሌላኛው ሙያ (ቀድሞ ይሰራበት ለነበረው ሙያ ) የስራ ልምድ መሆን ይችላል·
.አንድ ባለሙያ መጀመሪያ የሙያ ፈቀድ ቢሰጠውም ከ3 ዓመት በኋላ ሙያ ፈቃዱን ለማሳደስ ሲመጣ በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ በሁለቱም ሙያ እየሰራ ከሆነ ስለመስራቱ ደግሞ ተገቢ እና ህጋዊ የሆነ የስራ ልምድ ማቅረብ ከቻለ የሙያ ፈቃድ ሊታደስለትና ሊሰጠው የሚችለው በሙያው መስራት ከቻለ ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን በሙያው መስራት ካልቻለ ትምህርቱ ሊረሳ ስለሚችል የሙያ ፈቃድ የማይታደስበት እንደሆነ ያብራራል ፡፡·
በተጨማሪም አንድ ባለሙያ ሶስትና ከዚያ በላይ ሙያ ያለው ቢሆንም ባለሙያው በቀን ሊሰራ የሚችለው 8 ሰኣት ነው፡፡ ባለሙያው በ3ቱ ሙያ ስራውን በአግባቡ 8 ሰዓት እንዳይሰራ ሰዓቱ ይገድበዋል፣ ውጤታማም አይሆንም ስለዚህ ትምህርቱን መማር ብቻ ሳይሆን በተማረበት ሙያ ማገልገል እችላለሁ ወይ የሚለውን ማጤን እንደሚያስፈልግ እና የጤና ሙያ እንደሌላው የሙያ አይነት ሳይሆን የሰው ህይወት ላይ ስለሚሰራ ለሰው ልጅ ትልቅ ቦታ ስለሚሰጥ በምንም መልኩ ሰው መጎዳት ስለሌለበት ለጥንቃቄ ሲባል አንዱ ሙያ ሊገደብ እንደሚገባ መመሪያው ይገልጻል፡፡
ለበለጠ መረጃ መመሪያውን እና አስፈላጊ መረጃዎችን www.aafda.gov et በሚለው ዌብ ሳይት ላይ ያስቀመጥን ስለሆነ ገብታችሁ ማንበብና ሙሉ መረጃ የምታገኙ መሆኑን ለመጠቆም እንወዳለን ፡፡
seledadotio

8 months ago