Logo
FastMereja
"The Chandler to my Monica" ማህደር ከበደ ቀለበት ማድረጓን ይፋ አደረገች!
#fastmereja I ​የ"ወቸው ጉድ" ፖድካስት አቅራቢ ማህደር ከበደ፣ የህይወቷን አዲስ ምዕራፍ የሚያበስር ታላቅ ዜና ለአድናቂዎቿ አጋርታለች። ማህደር የቀለበት ስነስርዓቷን አስመልክቶ በማህበራዊ ገጿ ባሰፈረችው ልብ የሚነካና በፈገግታ የታጀበ መልዕክት፣ የትዳር አጋሯን በታዋቂ የፊልም ገጸ-ባህሪያት መስላ ገልጻዋለች።

​ማህደር ለትዳር አጋሯ ያላትን ጥልቅ ፍቅር በታዋቂዎቹ Friends እና How I Met Your Mother ተከታታይ ፊልሞች ውስጥ ባሉ የማይነጣጠሉ ጥንዶች መስላ እንዲህ ብላለች፡-

​"He is my lobster, the Chandler to my Monica, the Marshall to my Lily and the Ying to my Yung."

​ይህ አገላለጿ በመካከላቸው ያለውን ጠንካራ ቁርኝትና መግባባት የሚያሳይ ሲሆን፣ በተለይ "Lobster" የሚለው ቃል በታዋቂው የሮስና ራሄል የፍቅር ታሪክ ውስጥ "ለዘላለም አብሮ የሚኖር የህይወት አጋር" የሚል ትርጉም እንዳለው ይታወቃል።

​ማህደር በፖድካስት ስራ በርካታ አድናቂዎችን ማፍራት የቻለች ሲሆን፣ ይህ የደስታ ዜና ከተሰማበት ቅጽበት ጀምሮ በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ የእንኳን ደስ አለሽ መልዕክቶች እየጎረፉላት ይገኛል።

​ማህደርና የህይወት አጋሯ ለጀመሩት አዲስ ጉዞ እኛም መልካም ምኞታችንን እንገልጻለን!

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.