Logo
Getu Temesgen
ኮሜዲያን ያሲኖ በሰይፉ ሾው

በዘሪሁን ተዝናኑ

★ መሞከር መሠረታዊ ነገር ነው።

★ የዛሬ ስምንት ዓመት አካባቢ የማለዳ ኮከቦች
የትወና ውድድሮ ላይ 5ኛ ወጥቻለሁ።

★ የሰካራም ካራክተር ስሰራ ጠጥተህ ነው እንዴ
የምትሰራው ይሉኝ ነበር።

★ አሁን አክቲንግ ላይ ለምሰራው ነገር የማለዳ ኮከቦች
የትወና ውድድር ጠቅሞኛል።

★ ደብረ ዘይት ላይ አስተናጋጅ ሆኜ ሰርቻለሁ።
የታክሲ ረዳት ሆኜም ሰርቻለሁ። ለሹፌሮችና
ለረዳቶች ትልቅ ቦታ አለኝ።

★ ቢሾፍቱ ላይ በባህል ተወዛዋዥነት ስድስት ዓመት
ሰርቻለሁ።

★ እነዚህ ሁሉ ሙከራዎች ያሲንን አሁን ያለበት ደረጃ
አድርሰውታል።

★ እየሞከርን ነው የተሰኘው ቪዲዮ መነጋገሪያ ሆኗል።

★ ተስፋ ያጡ ሰዎች ተስፋ እንደሚያገኙ አምናለሁ።

★ ችግር የሚያጠቃው የተቀደደ ልብስ የለበሰ ሰው
ብቻ አይደለም።

★ ሶሻል ሚዲያ ላይ ኮሜዲ ብቻ አልሰራም።
የሚነሱ የሚያጋጩ ሀሳቦችን ማከም እፈልጋለሁ።

★ በሶሻል ሚዲያውም ሆነ በአርቱ ገንዘብ አልሰራም።

★ ብዙዎቹ ሰዎች በሶሻል ሚዲያ ገንዘብ የማገኝ
ይመስላቸዋል።

★ አንድ ሚሊዮን ተከታይ ያለኝ ልጅ እናቴ ስትቸገር
ሳይ ልቤ ይሰበራል።
★ ሌሎች በትንሽ ፎሎወር ገንዘብ ያገኛሉ።
ሶሻል ሚዲያ ላይ የሆኑ ቲሞች አሉ።

★ እናቴን ልጅሽ ደረሰልሽ ይሏታል። እውነታው ግን
አልደረስኩም።

★ እናቴ ደስተኛ ናት። ደረስክልኝ ትለኛለች።
ጊዜው እየደረሰ ነው ኢንሻ አላህ !

★ አንድ ሚሊዮን ተከታይ ስገባ ስልክ የለኝም።
በሰው ስልክ ነው የምቀርፀው።

★ ችግሮ ነዳጅ ነው ሀይል ይሆንሃል።

★ ማሰራት የሚፈልጉ ካምፓኒዎች ቢያሰሩኝ አላህ የሰጠኝ
አቅም አለኝ። አላምዱሊላሂ የሰው ፍቅር አለኝ።

★ ለሚያልፍ ጊዜ የማይሆን ነገር ማድረግ አልፈልግም።

★ ያመንኩት ጌታ ነው እዚህ ያደረሰኝ።

★ ከልጅነቴ ጀምሮ ፑሻፕ እሰራለሁ። ስፖርት በደንብ
ነው የምሰራው።

★ ሲክስ ፓኬን አይተው ይዋጣልን ይሉኛል። እኔ ግን
ገንዘብ ቢዋጣልኝ ነው ደስ የሚለኝ።

★ ሱሴ ማንበብ ነው።

★ መገኘት የሌለብኝ ቦታ ተገኝቼ አውቃለሁ።

★ ኢትዮ Fm ሬዲዮ ላይ ከድርሹ ዳና ጋር ወደ ሁለት ዓመት ያህል ሰርቻለሁ።

★ በልጅነት ዕድሜዬ አርቲስት እንደምሆን አውቅ ነበር።

★ አምስት ኪሎ ቅድስተ ማርያም ቤ/ክርስቲያን ግንብ
ስር አድሬ አውቃለሁ።

★ ረሃብ ይደብራል። ረሃብ ደስ አይልም።

★ የተሰራች ሴት አላህ ከሰጠኝ አገባለሁ።

★ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን አለም ላይ
መታወቅ እፈልጋለሁ።

★ ለተቸገሩ ሰዎች ጥላ መሆን እፈልጋለሁ።

★ ፌመስ ሆኜ ብድር የሌለብኝ ሱቅ የለም።

★ አባቴ አቶ ረዲ በጣም ጠንካራ እና ተጨዋች ሰው ነው።
አባቴ ዱቄት እየተሸከመ ነው ያሳደገን።

★ የደሃ ልጅ ስትሆን ሀዘንህ ይረክሳል።

★ የጭብጨባ ጉዳይ ብዙም ልቤን አይወጥረውም።
የስድብ ጋጋታም አዕምሮዬን አይነካውም።

★ አርቱ ላይ በፊልም ኢንዱስትሪው የሚያግዝህ ሰው
የለም። ፊልሙ ላይ የእነ እንትና የእነ እንትና የሚባል
ግሩፕ አለ።

★ እናቴ ስድስት ሜትር የተቆፈረ ጉድጓድ ውስጥ
አዳልጧት ወድቃ ታውቃለች።

★ ወጣቶች ስኬታማ መሆን ይፈልጋሉ። ምክንያቱም
ለፍተው ፣ ደክመው ያሳደጓቸውን ወላጆች መደገፍ
ይፈልጋሉ።

★ ትምህርት ቤት ስድስቱንም ክፍለ ጊዜ ግጥም ነበር
የምፅፈው።

★ አንቲ ቲዩብ በተሰኘው የራሴ ዩቲዩብ ቻናል ላይ አምስት
የአንድ ሰዓት ስታንዳፕ ኮሜዲዎች አሉ።

Comedian Yasino ከማለዳ ኮከቦች የትወና ውድድር
ጊዜ ጀምሮ ለኪነጥበብ ትልቅ ፍቅርና አቅም ያለህ ልጅ ነህ።
እየሞከርኩ ነው የሚለውን ትልቅ መልዕክት የሚያስተላልፈውን የአጭር ደቂቃ ቪዲዮ ሳይ አንተ ከምን
ተነስተህ የት እንደደረስክ የሚያሳይ የጠንካራ ወጣት
ተምሳሌት ነህ።
ፈጣሪ ያሰብከውን ሁሉ ያሳካልህ !

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.