Logo
SeledaPost
የአለም ውድ ወተት፡ የአይጥ ወተት!

​በአለም ላይ ውዱ ወተት የትኛው እንደሆነ ያውቃሉ? ላም፣ ግመል ወይስ ሌላ? መልሱ የአይጥ ወተት ነው!

​📌 ዋጋው ስንት ነው?
አንድ ሊትር የአይጥ ወተት ከ $22,000 (ከ3. 4 ሚሊዮን ብር በላይ) ያወጣል።

ይህም በአለም ላይ ካሉ ፈሳሾች ሁሉ ውድ ከሚባሉት አንዱ ያደርገዋል።

​🔬 ለምን ጥቅም ላይ ይውላል?

አይጥ የምትታለበው ለምግብነት ሳይሆን ለረቂቅ የህክምና ምርምር ነው። ሴት አይጦች በጄኔቲክ ማሻሻያ አማካኝነት ላክቶፌሪን (Lactoferrin) የተባለ የሰው ልጅ የፕሮቲን አይነት እንዲያመርቱ ይደረጋል። ይህ ፕሮቲን፦
👉​ልዩ ለሆኑ መድኃኒቶች ዝግጅት።
👉​የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም ለማጠናከር።
👉​ለጨቅላ ህፃናት አልሚ ምግቦች እና
👉ለካንሰር ህክምና ግብዓትነት ያገለግላል።

​🧪 ለምን ተወደደ?
አንድ ሊትር ወተት ለማግኘት ብቻ ወደ 4,000 የሚጠጉ አይጦችን በልዩ ጥበብ ማለብ ያስፈልጋል። ሂደቱ እጅግ አድካሚ እና ከፍተኛ የላቦራቶሪ ቴክኖሎጂን የሚጠይቅ በመሆኑ ዋጋው እንዲንር አድርጎታል።

ይህ አስገራሚ ጥናት የተካሄደው በሩሲያ የጂን ባዮሎጂ ተቋም (Institute of Gene Biology) ሲሆን፣ በተለያዩ የሳይንስ መጽሔቶችና ጥናቱ ታትሟል።

seledadotio
seledadotio
8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.