Logo
Getu Temesgen
አራቱ የፍትህ አካላት የቅንጅት ስራ
(ፖሊስ፣አቃቢ ህግ፣ፍርድ ቤት፣ማረሚያ ቤት)

የኢፊድሪ ወንጀል ህግ እና ወ/መ/ህ/ስ/ስነስረአት
ጠበቃና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው 0983337690,0929101037

የጹሁፉ አላማ #ethiopia | ፍትህ ለሰው ልጆች እጅግ አስፈላጊ ከመሆኑ የተነሳ የፍትህ ስረአቱ የዘመነ እና የሚያረካ እንዲሆን የፍትህ ተቋሟት በተሟላ መንገድ ተሰናድተው ጉዳዮችን ተቀበለው እንደተሰጣቸው ስልጣንና ኀላፊነት ከግብ ሊያደርሳቸው መገኘት ያለባቸው ቁመና ላይ ሊገኙ ያስፈልጋል። በዚህ ጽሁፍ የምንዳስሰው የፍትህ ተቋሟት ሚና እና ቅንጅት ለተሻለ ፍትህ የሚያደርጉትን ተቋማዊ ሰንሰለት ነው።

1. የፖሊስ ተቋም

የፖሊስ ተቋም ዘርፈ ብዙ ኃላፊነት ያለበት ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ወንጀልን መከላከል፣ሰላምን ማስፈን፣ወንጀለኞችን ለህግ ክፍል ማቅረብ፣ የወንጀል ምርመራ ማድረግ ዋነኛዎቹ ናቸው። በዚህች ንኡስ ጽሁፍ ውስጥ የምንመለከተው ግን የወንጀል ምርመራን በተመለከተ ነው። የወንጀል ምርመራ በአቃቢ ህግ እየተመራ ለምርመራ በበቁ መርማሪ ፖሊሶች የሚካሄድ ሲሆን ከአቤት ባይ፣ከአመልካች ወይም ከጠቋሚ መረጃን ተቀብሎ ለምርመራ መነሻ የሆነውን ነገር ጥንቃቄ በተሞላበት አካሄድ በጥበብ በተቀናጀ አካሄድ ህገመንግስታዊ የሰብአዊ መብት በጠበቀ መንገድ ጥፋተኛው በመጥራት ከጠፋም ለመቅረብ እንቢተኛ ከሆነ ከፍርድ ቤት በወ/መ/ህ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 53 መሠረት መያዣ በማስወጣት እንዲያዝ ከተደረገ በኋላ አስፈላጊ ሲሆን የጊዜ ቀጠሮ በፍርድ ቤት 53 መሠረት በመጠየቅ ምርመራ ውን በአግባቡ እንዲወጣ ይጠይቃል። ይህም አላማው ቢወጣ ማስረጃን ሊያጠፋ ወይም ለምርመራ መሰናክል ይሆናል ተብሎ ሲገመት ወይም ለምርመራው ውጤት ይረዳ ዘንድ ተብሎ ነው። ምርመራው ባለቀ ጊዚ ለአቃቢ ህግ የምርመራ ፋይሉን ለአቃቢ ህግ ያስረክባል። አቃቢ ህግ ምርመራው ገና መሆኑን የተረዳው እንደሆነ አቅጣጫ ሰጥቶ እንዲቀጥል ያደርጋል።

2. የፍትህ ሚኒስተር ተቋም

የፍትህ ሚነስተር ተቋምን ዋናውን ሚና የያዘው አቃቢ ህግ ነው። አቃቢ ህግ ክስ ያዘጋጃል፣የክስ ምርመራ ይመራል፣በፍርድ ቤት ቆሞ ይከሳል ይከራከራል ያስወስናል፣ቅጣት መፈጸሙን ይከታተላል ።

ይህን በአጭሩ የገለጽን ሲሆን ከላይ ፖሊስ በምርመራ ሂደቱ የተወጣን ድርሻ ለአቃቢ ህግ ካስረከበ በኋላ አቃቢ ህግ ያስከስሳል ወይንስ አያስከስስም የሚለውን ወስኖ የሚያስከስስ ከሆነ ክስ አዘጋጅቶ ፍርድ ቤት ያቀርባል ተከሳሽ በቀረበበትም ሆነ በሌለበት እንደ ህግ አግባብነቱ ተከራክሮ ያስወስናል። አላግባብ ነጻ ከሆነ በይግባኝ እንዲሻርለት ይጠይቃል።

3. ፍርድ ቤት

የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013
ፍርድ ቤት በአቃቢ ህግ የቀረበለትን ክስ ከመጥርያ ጋር በአቃቢ ህግ በኩል ለተከሳሽ እንዲደርስ ያደርጋል። የተከሳሽ እምነት ክህደት ቃል ተጠይቆ በግልጽ ካመነ ወዲያው ፍርድና ቅጣት ይሰጣል። ካላመነ አከራክሮ ማስረጃ ሰምቶ ፍርድ ይሰጣል። ነጻ ከሆነ በዚህ አግባብ ውሳኔ ይሰጣል። ጥፋተኛ ከተባለ ማቅለያና ማክበጃ ሰምቶ የቅጣት ውሳኔ ሰጥቶ የእስራት እና/ወይም የገንዘብ መቆጮ እና/ወይም የግዴታ መቀጮ ሰበአዊ መብቱን በማይጋፋ መልኩ ውሳኔ ይሰጣል። አፈጻጸሙን አቃቢ ህግ ይከታተላል። ወ/መ/ህ/ስ/ስነስረአት ህግ ቁጥር 195

4. ማረሚያ ቤት

የማረሚያ ቤቶች አዋጅ ቁጥር
ፍርድ ቤት በእስራት ውሳኔ ያስተላለፈውን ማረሚያ ቤት እንዲያስፈጽም ትእዛዝ ይጽፍለታል። ማረሚያ ቤቱም በተሰጠው የህግ ስልጣን መሠረት በፍርዱ መሠረት ያስፈጽማል።

ከሚያስፈጽመው አንጻር በጥቂቱ ስናነሳ

1. የጽኑ እና ቀላል እስራት ለተቀጡ ማረፊያ ቤቶችን በመለየት ያስፈጽማል። ጽኑ እስራት ፍርደኞች በባህሪያቸው አደገኛ የወንጀል ባህሪ ያለባቸው ናቸው ተብሎ ይገመታል።(የኢፊድሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 106) ቀላል እስራት የተላለፈባቸው ፍርደኞች በባህሪያቸው ከጽኑ እስራት ፍርደኞች አደገኝነታቸው መለስ ያለ ነው ተብሎ ይገመታል።(የኢፊድሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 208) የወጣት ጥፈተኞችን ማረፊያ፣ የእናት አጥቢዎች ፍርደኞች፣በእድሜ የገፉ ፍርደኞች ከሰብአዊ መብት አጠባበቅ አንጻር አስፈላጊውን ሁሉ በመፈጸም፣ከመማር መብት፣የመሥራት፣የፈጠራ መብት ፣ ሰርቶ ገንዘብ ከማግኘት መብት እንዲሁም የህግ ግንዛቤ በመስጠት አእምሮአቸው እንዲታረም አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ ያስፈልጋል።

5. ሲጠቃል
አራት የፍትህ አካላት ለአንድ የፍትህ ግብ ተቀናጅተው የሚሰሩበት የፍትህ ስረአት ነው።
https://www.facebook.com

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.