የሰይፍ አል-ኢስላም ጋዳፊ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በውጥረት ተጠናቀቀ
ባለፈው ማክሰኞ ባልታወቁ ታጣቂዎች የተገደለው የቀድሞው የሊቢያ መሪ ሙአመር ጋዳፊ ልጅ የሰይፍ አል-ኢስላም ጋዳፊ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት በባኒ ዋሊድ ከተማ ተፈጽሟል።
በቀብሩ ላይ የታዩ ዋና ዋና ክስተቶች፦
📍 ያልተለመደ ግርግር፦ በሺዎች የሚቆጠሩ የሟች ደጋፊዎች "የሰይፍ አል-ኢስላም አስከሬን በይፋ ታይቶ ይረጋገጥ፤ ሳጥኑ ይከፈት!" በማለት ከፍተኛ ጥያቄ ቢያቀርቡም የጸጥታ ኃይሎች ሳይፈቅዱ ቀርተዋል።
📍 ወታደራዊ ጥበቃ፦ የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ በጠቅላይ ሚኒስትር አብዱል ሃሚድ ድበይባ መንግሥት ጥብቅ ቁጥጥር ሲደረግበት ውሏል።
📍 ያልተመለሱ ጥያቄዎች፦ ሰይፍ አል-ኢስላም በዚንታን ከተማ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በድንገት መገደሉን ተከትሎ፣ እስካሁን ገዳዮቹ እነማን እንደሆኑ አልታወቀም።
ሰይፍ አል-ኢስላም በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ይፈለግ የነበረ ቢሆንም፣ በሊቢያ ፖለቲካ ውስጥ ዳግም ለመሳተፍ ሲንቀሳቀስ መቆየቱ ይታወሳል።

8 months ago