ጾመ ነነዌ🙏
ንስሐቸው በከንቱ እንዳልቀረ አስረድቷቸዋል
ነነዌ ከተማ በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ ስትሆን መሥራቿም ናምሩድ ነው፡፡ የነነዌ ሕዝብ ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ቢበዛም በከንቱ ሊያጠፋቸው አልወደደምና ነቢዩ ቅዱስ ዮናስን እንዲያስተምራቸው ላከው፡፡ እርሱ ግን “አንተ መሐሪ ነህና ነነዌ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ብትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ” ብሎ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡ እግዚአብሔርም ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧ በማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩ ነጋድያንም ያላቸውን ሀብት ወደ ባሕሩ መጣል ጀመሩ፡፡ ነቢዩ ዮናስ ጥፋቱን ተገንዝቦ “ማዕበሉ በእኔ ምክንያት የመጣ ስለሆነ ንብረታችሁን ሳይሆን እኔን ወደ ባሕር ጣሉኝ” አላቸው፣ ዮናስንም ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡
ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ ነባሪ ዮናስን ውጦት ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ወደ ነነዌ አደረሰው፡፡ እግዚአብሔር የቅል ተክል ጥላ አድርጎለት አረፈ፡፡ ተኝቶ ሲነሳም ተክሉን ትል በልቶት ደርቆ ስላየ አዘነ፡፡ እግዚአብሔርም በትንቢተ ዮናስ 4÷11 እደተጻፈው “አንተ ላልደከምክበትና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ፣ ግራና ቀኛቸውን የማያውቁ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ እንደምን አያሳዝኑኝምን?” ብሎታል፡፡ ዮናስም የነነዌ ሰዎችንም “ንስሐ ግቡ” እያለ መስበክ ጀመረ፡፡ የነነዌ ሰዎችም ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ይቅር ብሎ ከጥፋት አድኗቸዋል፡፡
ሐሰት እንዳይባልም እሳቱ እንደ ደመና ሆኖ ከላይ ታይቶአል፡፡ የታላላቁ ዛፍ ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ አድርቆ ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ ንስሐቸው በከንቱ እንዳልቀረ አስረድቷቸዋል፡፡
ገዳማውያን ይህን ጾም ስለሀገራችን ሰላምና፣ ስለቅድስት ቤተ ክርስቲን አንድነት በመጾምና በመጸለይ በተጋድሎ ያሳልፉታል፡፡ በእነዚህ የጾም ቀናት ገዳማውያንን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና ከበረከታቸው እንሳተፍ፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

8 months ago