ቀርከሃ ለልብ ጤና እና ለስኳር ቁጥጥር ጠቃሚ የሆነ አዲስ "ሱፐርፉድ" መሆኑ ተገለጸ
እስያ ውስጥ ለዘመናት በምግብነት ሲያገለግል የቆየው የቀርከሃ ቡቃያ፣ ለልብ ጤና፣ ለደም ስኳር ቁጥጥር እና ለሰውነት በሽታ መከላከል አቅም እጅግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው አዲስ "ሱፐርፉድ" መሆኑን ሳይንቲስቶች ገለጹ።
በእንግሊዝ የሚገኘው የአንግሊያ ረስኪን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ያካሄዱት አዲስ ጥናት እንደሚያሳየው፣ የቀርከሃ ቡቃያ ወይም ከእሱ የሚወጡ ንጥረ ነገሮች በሰውነት ውስጥ ያለውን የኮሌስትሮል እና የስብ መጠንን ለመቀነስ ይረዳሉ። በተጨማሪም በሰውነት ውስጥ የሚፈጠርን ቁስለትን የመከላከል እና የደም ስኳር መጠንን የማመጣጠን ከፍተኛ አቅም እንዳላቸው በጥናቱ ተረጋግጧል።
የቀርከሃ ቡቃያ የስብ መጠኑ አነስተኛ ቢሆንም፣ በፕሮቲን፣ በተለያዩ ፋይበሮች፣ በአሚኖ አሲድ፣ እንዲሁም እንደ ሴሊኒየም እና ፖታሺየም ባሉ ማዕድናትና ቪታሚኖች የበለጸገ ነው። ቀደምት የጥናት ውጤቶች እንደሚያመለክቱት፣ ቀርከሃ በጨጓራና አንጀት ውስጥ የሚገኙ ጠቃሚ ባክቴሪያዎችን በመመገብ ለተስተካከለ የምግብ መፈጨት ሥርዓት ከፍተኛ ድጋፍ ይሰጣል።
ይሁን እንጂ ተመራማሪዎቹ አንድ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል። የቀርከሃ ቡቃያ ለምግብነት ከመዋሉ በፊት በትክክል መዘጋጀትና መብሰል ይኖርበታል። አንዳንድ የቀርከሃ ዝርያዎች ጥሬያቸውን ወይም ሳይበስሉ ሲበሉ "ሳይናይድ" የተሰኘ መርዛማ ንጥረ ነገር ሊያመነጩ ይችላሉ። በተጨማሪም በአግባቡ ያልበሰለ ቀርከሃ የታይሮይድ ሆርሞን ምርትን በማስተጓጎል ለእንቅርት በሽታ ተጋላጭነትን ሊጨምር እንደሚችል ተጠቁሟል።
seledadotio

9 months ago