4ኛው አገር አቀፍ የልህቀት መድረክ በአዲስ አበባ ተካሄደ
#fastmereja I የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ያዘጋጀው 4ኛው የልህቀት መድረክ (Excellence Summit) ዛሬ ሐሙስ ጥር 14 ቀን 2018 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል ተካሄደ።
መድረኩ ጥራት ያለው ምርትና አገልግሎትን ለማበረታታት፣ የጥራትን ጽንሰ-ሐሳብ ለማስረጽ እና ጥራት የአገሪቱ ባሕል እንዲሆን ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ ነው። በዕለቱም በአገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ውድድር ተሳትፈው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ የመንግሥትና የግል ተቋማት ለስኬት ያበቋቸውን ምርጥ ተሞክሮዎች ለሌሎች ድርጅቶች አካፍለዋል።
በመርሐ-ግብሩ ላይ የዘርፉ ምሁራን ስለ ጥራትና ልህቀት ያጠኗቸውን የምርምር ግኝቶች ያቀረቡ ሲሆን፣ ጥራትን የአገሪቱ መለያ ለማድረግ የልህቀት ሞዴሉ (EQA Excellence Model) ስላለው ሚና የሚያጠነጥን የፓናል ውይይትም ተካሂዷል።
የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ባዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች፣ ተቋማት እርስ በእርስ የሚገናኙበትና የሥራ ትስስር (Networking) የሚፈጥሩበት ዕድል ተመቻችቶላቸዋል። ድርጅቱ ዓለም አቀፍ የጥራት መለኪያዎችን መሠረት በማድረግ በአገራችን በማምረትና አገልግሎት በመስጠት የተሰማሩ ተቋማትን በማወዳደርና ዕውቅና በመስጠት የሚታወቅ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል።
የዛሬው የልህቀት መድረክም ድርጅቶች ካሏቸው ስኬታማ ተሞክሮዎች እንዲማሩና ጥራትን እንደ መመሪያ እንዲጠቀሙ ትልቅ መነቃቃት የፈጠረ መሆኑ ተገልጿል።

5 months ago