ታላቁ የሲ.ኤም.ሲ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ጥር 16 እና 17 ሊመረቅ ነዉ!
#fastmereja : ታላቁ የሲ.ኤም.ሲ ደብረ ጽባህ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ግንባታው ተጠናቆ ለምረቃ መብቃቱን የደብሩ አስተዳደር በዛሬው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አብስሯል።
የዛሬ 30 ዓመት በ1986 ዓ.ም. ከፍልውሃ አካባቢ በልማት ተነስተው ወደ አልታድ የመጡ ምዕመናን፣ በወቅቱ ቤተ ክርስቲያን በአቅራቢያቸው ባለመኖሩ ለእርጅናና ለእንግልት ተጋልጠው ነበር። ሆኖም ግን የነዋሪዎቹ ጽናትና የአባቶች ተነሳሽነት ታክሎበት፣ በነ አቶ ዳዲ ቡልቃ እና አቶ ሰቦቃ በጎ ፈቃደኝነት በተሰጠ የእርሻ መሬት ላይ በ"ሳጣራ" ቤት ተጀመረ።
ያ "የሳጣራው ሚካኤል" እየተባለ የሚጠራው ትንሽ መቃኞ፤ በኋላም በደገኛው አባት በአቶ ቁምላቸው ገብረሥላሴ ሙሉ ወጪ በሕንጻ ተተክቶ ለዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። ዛሬ ግን ያ ታሪክ ተቀይሮ በአዲስ አበባ ሰማይ ሥር ደምቆ የሚታይ ግዙፍ ካቴድራል ሆኗል።
ቁመትና ምሳሌ፦ ዋናው ጉልላት የእመቤታችንን ዕድሜ ለመዘከር 64 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን፣ በሀገራችን ካሉ ረጅም አብያተ ክርስቲያናት ቀዳሚው ነው።
ዲዛይን፦ የክብ፣ የዋሻ እና የሰቀላማ ቤተ ክርስቲያን አሠራሮችን በአንድ ላይ አዋህዶ የያዘ ድንቅ የጥበብ ውጤት ነው።
የመያዝ አቅም፦ በአጠቃላይ 7,000 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን፣ በአንድ ጊዜ 10,000 ምዕመናንን ማስተናገድ ይችላል።
ልዩ ገጽታ፦ በሰማያዊ ጣሪያው ላይ ያሉት መብራቶች የሰማይ ከዋክብትን የሚመስሉ ሲሆን፣ እስከ መስቀሉ ድረስ መውጫ ያለውና ከተማዋን ቁልቁል የሚያሳይ ስፍራ አለው።
ጥር 16 ቀን 2018 ዓ.ም፦ ከቀኑ 7:30 ጀምሮ ታላቅ የዋዜማ ጸሎትና የንግሥ በዓል።
ጥር 17 ቀን 2018 ዓ.ም፦ ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳትና እንግዶች በሚገኙበት ታላቅ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ይከናወናል።

9 months ago