Logo
YenetaTube
የቤት እድለኞች የሐሰተኛ መረጃ ሰለባ እንዳይሆኑ ቢሮው አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ ሰጠ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ20/80 እና 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራሞች የተመዘገቡ ዜጎች በማህበራዊ ሚዲያ በሚሰራጩ የተሳሳቱ መረጃዎች እንዳይታለሉ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላለፈ።

ቢሮው ይህንን ጥሪ ያስተላለፈው "የምዝገባ ቆይታችሁን አረጋግጡ" እና "የምዝገባ ሁኔታችሁን ነቁ ወይም አክቲቭ አድርጉ" በሚሉ ማታለያዎች ተመዝጋቢዎች ወደ ቢሮው እየመጡ አላስፈላጊ እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን በማስተዋሉ ነው።

በመሆኑም ማንኛውም ተመዝጋቢ የሐሰተኛ መረጃ ሰለባ ከመሆን ይልቅ የራሱን የቆጠባ ሂሳብ ቁጥር ብቻ በመጠቀም ካለበት ሆኖ በድረ-ገጽ ምዝገባውን ማረጋገጥ እንደሚችል ቢሮው አረጋግጧል።

በተለይ ሰሞኑን በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚሰራጩ የሐሰት ጥሪዎች ተመዝጋቢዎችን ለከፍተኛ እንግልትና ለተጨማሪ ወጪ እየዳረጉ መሆኑን የገለጸው ቢሮው ዜጎች ያለምንም የጊዜ ገደብ መረጃቸውን ማግኘት እንደሚችሉ አስታውቋል።

ተመዝጋቢዎች ወደ ቢሮው በአካል በመምጣት መሰለፍ ሳያስፈልጋቸው [http://aahdab.et/saving](h... የተሰኘውን የቢሮውን ይፋዊ ድረ-ገጽ በመጠቀም ያለበትን ደረጃ በቀላሉ ማወቅ ይችላልተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም ማንኛውም ወቅታዊ መረጃ የሚሰራጨው በቢሮው የፌስቡክ፣ የቴሌግራም፣ የቲክቶክና የዩቲዩብ ገጾች ብቻ በመሆኑ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተመክሯል።
#አሐዱ

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.