"ትራምፕ ካልቸኮሉ ግሪንላንድ የሩሲያ አካል ልትሆን ትችላለች" ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ
የሩሲያ ብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ፤ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአርክቲክ ደሴት የሆነችውን ግሪንላንድን ለመቆጣጠር ፈጣን እርምጃ ካልወሰዱ፣ ደሴቷ ወደ ሩሲያ ለመቀላቀል ልትወስን ትችላለች ሲሉ በፌዝ መልክ አስጠነቀቁ።
ሜድቬዴቭ ይህን ያሉት ትራምፕ ግሪንላንድን ለአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት ወሳኝ ናት በማለት ለመግዛት ወይም ለመቆጣጠር ዳግም ጥረት እያደረጉ ባሉበት ወቅት ነው።
ሜድቬዴቭ "ማክስ" (በተሰኘው የሩሲያ ማህበራዊ ድረ-ገጽ ላይ ባሰፈሩት አስተያየት፤ "ትራምፕ መቸኮል ይኖርበታል። ባልተረጋገጠ መረጃ መሰረት በጥቂት ቀናት ውስጥ ድንገተኛ ህዝበ ውሳኔ ሊካሄድ ይችላል፤ በዚህም 55,000 የሚጠጉ የግሪንላንድ ነዋሪዎች ወደ ሩሲያ ለመቀላቀል ሊመርጡ ይችላሉ" ብለዋል።
አክለውም "ያን ጊዜ ሁሉም ነገር ያበቃል። በአሜሪካ ሰንደቅ ዓላማ ላይ አዲስ ኮከብ አይጨመርም" ሲሉ በሳቅ የታጀበ (Sarcastic) አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ሜድቬዴቭ ግሪንላንድ የሩሲያ "90ኛው የፌዴራል አካል" ልትሆን እንደምትችልም ጠቁመዋል።
ምንም እንኳን ሩሲያ በይፋ ግሪንላንድ ላይ የይገባኛል ጥያቄ ባይኖራትም፣ የአርክቲክ ቀጠና ለሀገሪቱ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን ትገልጻለች። የክሬምሊን ባለስልጣናት የሜድቬዴቭን ንግግር እስካሁን በይፋ ባያረጋግጡም፣ ቀደም ሲል በግሪንላንድ ዙሪያ የሚካሄደው ክርክር "ድራማዊ" መሆኑን ገልጸው ነበር።
የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ የሜድቬዴቭ አስተያየት ሆን ተብሎ በአሜሪካ እና በአውሮፓ አጋሮቿ መካከል ያለውን አለመግባባት ይበልጥ ለማባባስ የታለመ የቃላት ጦርነት አካል ነው።

9 months ago